Burundi President
Burundi President

ቡሩንዲ ከሶማሊያ አትዋሰነም። ግን ደግሞ ሶማሊያን የፖለቲካ መደራደሪያ አድርጋታለች። የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ፒየር ኑክሩንዚዛ ለሶስተኛ ዙር በስልጣን ለመቆየት መወሰናቸው ተከትሎ በሀገሪቱ የእልቂት አደጋ የጋበዘ ቀውስ አንዣቧል። አለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይም የአፍሪቃ ህብረትና የመንግስታቱ ድርጅት በቡሩንዲ ሰላም አስከባሪ ለማሰማራት ሀሳብ ቢያቀርቡም የቡሩንዲ መንግስት አልተቀበለውም። እንዳውም ያለፈቃዴ ሰላም አስከባሪ ከተሰማራ መልሼ እወጋዋለሁ ሲል አስጠንቅቋል። ቡሩንዲ በሶማሊያ ሰላም አስካባሪ ወታደሮችን አሏት። እናም ከአፍሪቃ ህብረት ጫና ሲበረታባት ወታደሮቿን ከሶማሊያ በማስወጣት ልትበቀል ትችላለች የሚለው ስጋት አሁን የሰመረ ይመስላል። የአፍሪቃ ህብረት በቡሩንዲ ሰላም አስካባሪ የማሰማራት ሀሳቡን አዘግይቶ ተጨማሪ ድርድር እንዲደረግ ወስኗል። ቻላቸው ታደሰ ያዘጋጀው ዘገባ እነሆ።

በቡሩንዲ የተከሰተው ቀውስ ዘጠነኛ ወሩን አስቆጥሯል፡፡ ከግጭቱ መቀስቀስ ወዲህ ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ200 ሺህበላይ የሚሆኑ ደግሞ ለስደ​​ት መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በታህሳስ ወር አጋማሽ በዋናከተማዋ ቡጁምብራ 87 ንፁሃን ዜጎች በአንድ ቀን መገደላቸው ደግሞ ስጋቱን አባብሶታል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ቀደም ብሎ ያሰማራውበሀገሪቱ ሰብዓዊ መብት ጥሰትን መፈፀሙን የሚያጣራው ቡድን ስራውን ባለፈው ታህሳስ ሲያገባድድ የዘፈቀደ ግድያዎችና ግርፋትንጨምሮ ሰብዓዊ ወንጀሎች መፈፀማቸውን ማረጋገጡን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ምንም እንኳን እርስ በርስ መወነጃጀሉ እንደቀጠለቢሆንም መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎች ጎሳዊ ግጭት የመቀስቀስ ሙከራ ሲያደርጉ እንዳልታዩ እና ግጭቱም ጎሳዊ መልክ እንዳልያገለልተኛ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

አፍሪካ ህብረት አምስት ሺህ ወታደሮች የሚይዘውን African Prevention and Protection Mission in Burundi ተብሎ የተሰየመውንሰላም አስከባሪ ኃይሉን ያለ መንግስት ፍቃድም ቢሆን ወደ በሀገሪቱ ለማሰማራት የወሰነው ባለፈው ታህሳስ ነበር፡፡ የቡሩንዲ መንግስትግን ህብረቱ ወታደሮቹን በግድ አሰማራለሁ ካለ እንደ “ወራሪ ሰራዊት” እንደሚታይ ሲዝት ቆይቷል፡፡ ህብረቱ በአንድ ሀገር የዘር ማጥፋት(ጅኖሳይድ)፣ የጦር ወንጀል ወይም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መኖራቸውን ካረጋገጠ ሲቪል ዜጎችን ከጥቃት ለመከላከልሲል በመተዳደሪያ ቻርተሩ መሰረት የመንግስት ፍቃድ ባይኖርም ጣልቃ የመግባት ስልጣን እንዳለው በመጥቀስ ሰላም አስከባሪ ሃይሉንከማሰማራት እንደማይቆጠብ እየገለፀ ነው፡፡ ህብረቱ እስካሁን ሉዓላዊ መንግስት ሳይፈቅድ ሰላም አስጠባቂ ጦር አሰማርቶ አያውቅም፡፡ያለ መንግስት ፍቃድ ሰራዊቱን ካሰማራ ግን ሰራዊቱ ገለልተኛ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት (peacekeeping mission) መሆኑ ቀርቶ ወገንተኛየውጊያ ተልዕኮ (peace enforcement) ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ምንም እንኳ በሱማሊያ መንግስት ግብዣ የተሰማራ ቢሆንምእስካሁን የህብረቱ ተዋጊ ኃይል ከአልሸባብ ጋር እየተፋለመ ያለው አሚሶም ብቻ ነው፡፡

አስራ አምስት የተባበሩት መንግስታት ፀጥታው ምክር ቤት አባላትንና ጋዜጠኞችን ያካተተው ልዑካን ቡድን ባለፈው ወር ለቀውሱመፍትሄ ለማፈላለግ በሀገሪቱ በአካል ተገኝቶ ጉብኝት አድርጓል፡፡ ልዑካን ቡድኑ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪኃይል መሰማራትን እንዲቀበሉ ግፊት ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ግን ሃሳብቡን ወዲያው ነበር ውድቅያደረጉት፡፡

 በፖለቲካዊ አጣብቂኝ ውስጥ የቆየው ህብረቱ አዲስ አበባ ላይ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደው የመሪዎች ጉባዔ ያለ መንግስት ፍቃድሰላም አስጠባቂ ሰራዊቱ የማሰማራት ዕቅዱን በመሰረዝ የፖለቲካ መፍትሄ አፈላላጊ ልዑካን ቡድን ብቻ ለመላክ ወስኗል፡፡

ከህብረቱ አባልሀገራት ውስጥ ድጋፍ በማሰባሰብ የቤት ስራቸውን የተወጡ የሚመስሉት ፕሬዝዳንቱ ከህብረቱ ጋር የገቡበትን እሰጥ አገባ በአሸናፊነት ተወጥተውታል፡፡ ውሳኔው በግዴታ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ማሰማራት ለህብረቱ የመጀመሪያው ከመሆኑ አንፃር ለተመሳሳይ ጣልቃገብነት በር ይከፍታል ብለው የሰጉ መሪዎች ጥቂት እንዳልሆኑም ግልፅ አድርጓል፡፡

ቡሩንዲ በአፍሪካ ህብረት አሚሶም ጥላ ስር እኤአ ከ2007 ጀምሮ በሱማሊያ ያሰማራችው ጦር ከአምስት ሺህ በላይ ሲሆን በብዛቱምሁለተኛው ነው፡፡ በአምስት ተቀያያሪ ምድብ ሰራዊት የተከፈለው የቡሩንዲ ጦር ሰራዊት በብዛትም ቢሆን በሁለተኛ ደረጃ ላይየሚቀመጥ ነው፡፡

ያኔ ሰላም አስጠባቂ ሰራዊት ታዋጣለች ተብላ ያልተጠበቀችው ቡሩንዲ ጦሯን ለአሚሶም የላከችው ኢትዮጵያ ጦሯንከሱማሊያ ለማስወጣት መወሰኗን ተከትሎ ነበር፡፡

የቡሩንዲ መንግስት ያንን እርምጃ የወሰደው ከ2005ቱ ሰላም ስምምነት መሰረት የቱትሲዎች የበላይነት እንዳለበት ከሚነገርለት ሰራዊት ላይ የወታደር ቅነሳ በማድረግ  ጣጣ ስለሚያመጣ የተወሰኑትን ወታደሮች ወደሱማሊያ መላኩ እንደሚሻል በማሰብ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በሌላ በኩል የውጭ ገንዘብ ድጋፍን ታሳቢ ያደረገ እንደነበርም የሚያስረዱታዛቢዎች አሉ፡፡

የቡሩንዲ ሰራዊት በሱማሊያ ከተሰማራ ጀምሮ ከአልሸባብ ጋር በርካታ ውጊያዎች ያደረገ ቢሆንም ምሽጉን ጥሎ በመሸሽና ለአልሸባብኃይሎች በማስረከብም ትችት ይቀርብበታል፡፡ ባለፈው ሃምሌ በቡሩንዲ ወታደራዊ ሰፈር ልዩ ስሙ ሌጎ በተባለ ቦታ በአልሸባብ በተሰነዘረድንገተኛ ጥቃት 60 ያህል ቡሩዲያዊያን ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን ወታደራዊ ጣቢያውንም የአልሸባብ ተወጊዎች ተቆጣጥረውታል፡፡

ኡጋንዳ እና ኬንያም በያዝነው ዓመት ከባድ ጥቃቶች የተፈፀሙባቸው ሲሆን ስኬታማዎቹ ጥቃቶቹም የአልሸባብ አዲሱ የደፈጣ ውጊያስልት አሚሶምን ብዙ ዋጋ እያስከፈለው ነው፡፡ ምንም እንኳ የኬንያ መንግስት ስትራቴጂያዊ ማፈግፈግ አድርጎ ቢያቀርበውም ጥቃቱግን የኬንያ ወታደሮችን ይዞታ አልሸባብ ተቆጣጥሮታል፡፡ የአልሸባብ ጥቃቶች እየጨመሩ በመሄዳቸውና በሴራሊዮን መውጣትየተፈጠረውን ክፍተት ለመሸፈን ኢትዮጵያ በቅርቡ ጦሯን ኪሲማዩ ወደብ ወደሚገኝበት እና ቀጠና ሁለት ተብሎ በሚታወቀውጁባላንድ ራስ ገዝ አካባቢ ለማስፈር ተገዳለች፡፡

 

ለአሚሶም ጦር ያዋጡ ሀገሮች ከውጭ ለሚደርስባቸው የተለያዩ ጫናዎች አሚሶምን እንደ መደራደሪያ  መጠቀማቸውአዲስ ነገር አይደለም፡፡ ቀደም ሲል ኡጋንዳ “ኤም 23” የተሰኘውን የኮንጎ አማፂ እንደምትረዳ ጠንካራ ኣለም ኣቀፍ ውንጀላዎችሲቀርቡባት በምላሹ ጦሯን ከሱማሊያ እንደምታስወጣ በመዛት ውንጀላው እንዲለዘብላት ለማድረግ ሞክራ ነበር፡፡ በውሳጣዊ ቀውስእየተናጠ ያለው የቡሩንዲ መንግስትም አፍሪካ ህብረት የሚያደርግበትን ተፅዕኖ እንዲያቆምለት “ጦሬን ከሱማሊያ አስወጣለሁ” ቢልህብረቱ፣ አሚሶምና የሱማሊያ መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገቡ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡፡

 

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለሦስተኛ ጊዜ ለምርጫ መወዳደራቸውን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ለቡሩንዲ ይሰጥ የነበረውን ወታደራዊ-ነክየገንዘብ ድጋፍ ባለፈው ግንቦት ማቋረጡ ባለፈው ሃምሌ በአልሸባብ ከተገደሉበት ወታደሮች ጋር ተዳምሮ ቡሩንዲ ጦሯን ከአሚሶምልታስወጣ እንደምትችል ተሰግቶ የነበረ ቢሆንም መንግስት ግን ምንም እርምጃ አለመውሰዱ በመጨረሻ ጠቅሞታል፡፡

ከአልሸባብ ጥቃት መጠናከር ባሻገር የአሚሶም ተልዕኮም ከተገመተው በላይ መራዘሙ ቡሩንዲን የሚተካ አፍሪካዊ ሀገር የማግኘቱንነገር አጠራጣሪ እንደሚያደርገው በሰፊው ይታመናል፡፡ በተለይ ሱማሊያ በያዝነው ዓመት ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀችባለችበት ወቅት የፀጥታው ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ስለማይቀር አሚሶም በተለይም የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ ጫና እንደሚኖርበት ጥርጥርየለውም፡፡ ሆኖም በዚህ ዓመት የአልሸባብ ጥቃት ሰለባ የሆኑት ኬንያና ኡጋንዳ በቅርቡ ሁለት ሺህ ተጨማሪ ወታደሮችን ለማዋጣትፍቃደኛ መሆናቸው ለአሚሶም መልካም ዜና ተደርጎ ተወስዷል፡፡

 

ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎች ያጠሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሀገሪቱ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የህብረቱን ውሳኔ ብቻ በመጠባበቅላይ እንደነበር ፍንጮች ነበሩ፡፡ አሜሪካና አውሮፓ ህብረትም የማዕቀብ ደጋፊዎች እንደሆኑ ውስጥ ውስጡን ሲናፈስ ቆይቷል፡፡ የህብረቱውሳኔ ግን በእነዚህ ውጥኖች ላይ በረዶ ቸልሶባቸዋል፡፡