Ethio-Telecom PR head Abdurhaman Ahmed
Ethio-Telecom PR head Abdurhaman Ahmed

ዋዜማ ራዲዮ-ወርቅ የምትጥል ዶሮ የሚለውንና የስርዓቱ ዋና የገቢ ምንጭ የሆነውን የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጥ ሀገሪቱን ከፍተኛ ገቢ ያሳጣታል። ስርዓቱን ከተቃውሞ ለመታደግ የሚደረገው የኣኢንተርኔት መቋረጥ በቢልየን ለሚቆጠር ገቢ መታጣት ሰበብ ሆኗል።
በጥራት አገልግሎት ከመስጠጥ ይልቅ ያለእንከን አገልግሎት ማቋረጥን ይበልጥ የተካነበት መሆኑን ያስመሰከረው ኢትዮ ቴልኮም በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውሃ ቀጠነ ምክንያት የኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎቶችን ድርግም ማድረግ የቀን ተቀን ስራው ሆኗል፡፡ ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ያቋረጠው አገልግሎት በአንዳንድ አከባቢዎች ሙሉለሙሉ ወደነበረበት አልተመለሰው፡፡ ይህ እርምጃው የዜጎችን ህገ-መንግስታዊ መብት የሚጋፋ ከመሆኑ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውም ከፍተኛ ነው፡፡ በቀን በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና የሚያስገባው ድርጅቱ በየምክንያቱ በሚያቋርጠው አገልግሎት ገቢው እንደሚጎዳ ጥያቄ ውስጥ አይገባም፡፡ ከህዝብ መዋጮ ባለፈ የአባይ ግድብ ዋንኛው የግንባታ በጀት የሚመደበው ከኢትዮ ቴሌኮም ትርፍ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ኤዶም ካሳዬ ዝርዝሩን ትነግረናለች- የድምፅ ዘገባውን እዚህ ያገኙታል አልያም ንባብዎን ይቀጥሉ

በኢትዮጵያ በብቸኝነት የቴሌኮምና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን የሚሰራው መንግስታዊ ተቁዋም ኢትዬ ቴሌ ኮም በየግዜው ኢንተርኔት እና የስልክ አገልግት የሚያቋርጥባቸው ምክንያቶች አሳማኝ በመሆናቸው እንደሁኔታው እየታየ የሚቀጥልበት መሆኑን ፍንጭ ሰጠ፡፡
ኢትዬቴሌኮም በብቸኝነት የያዘውን አገልግሎት በተደራጀ መንገድ ማቅረብ አልቻለም ተብሎ ከሚቀርብበት ስሞታ በተጨማሪ ከአላማው ውጪ በመንግስት ትዕዛዝ በየጊዜው ቴሌፎንና ማህበራዊ ድረ ገጾችን መዝጋቱ ሕዝቡ በተቁዋሙ ላይ ያለው እምነት እየተመናመነ እንዲሔድ ማድረጉ ይነገራል፡፡

በቅርቡ በአ/አ እና በኦሮሚያ አካባቢዎች በተነሳው ተቃውሞ እንዲሁም የከፍተኛ ት/ት መግቢያ ፈተና ተሰረቀ በሚል ምክንያት ተቁዋሙ ህዝቡን ሳያከብርና የንግድ እና የስራ ባህሪያቸው ድርጅቱ በሚሰጠው አገልግሎት ለይ መሰረት ያደረጉ ተቋሞችን ሳያማክር እንዲሁ ማቋረጡ ይታወሳል፡፡ አገልግሎቶቹ ሙሉ በሙሉ ያለተመለሱባቸው አከባቢዎችም አሉ፡፡
ስለዚሁ ጉዳይ የተጠየቁት የኢትዮ ቴለተኮም የኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ እንዲሕ ብለዋል፡፡


ኢትዬ ቴሌኮም ያለ ተግባሩና ሚናው አገልግሎቱን ባቁዋረጠባቸው ጊዜአት ምን ያህል ገንዘብ አጥቶ ይሆን ለሚለው ጥያቄ ሃላፊው የሰጡት ምላሽ ሒሳቡን አላሰላነውም የሚል ነው።

ይህም ቢሆን በተያዘው በጅት አመት ከደንበኞቹ 28 ቢሊዬን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዬ ቴሌኮምን ወደ ግል ይዞታነት እንዲያዞሩ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለቀረበላቸው ጥያቄ የምትታለብን ላም ማን ያርዳታል የሚል ምላሽ በመስጠት ተቁዋሙን ወደ ግል ይዞታነት መንግስታቸው በምንም አይነት እንደማይቀይረው በተናገሩት መሰረት በብቸኝነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። እሳቸውን ተክተው በስልጣን ላይ ያሉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝም ለተመሳሳይ ጥያቄ ተመሳሳይ መልስ ነበር የሰጡት፡፡
አቶ አብዱራህማን የድርጅቱ ዋንኛው ገቢ ምንጭ የተንቀሳሽ ስልክ አገልግት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡


በአሁኑ ጊዜ ከመደበኛ የስልክ መስመር አገልግሎት ውጪ 46 ሚሊዬን የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት የሚናገረው ኢትዬ ቴሌኮም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ከ2 አመት በፊት የጀመረውን ስራ ማጠናቀቅ እቅቶት ከጊዜው አንድ አመት በላይ እሳልፎአል።

ተቁዋሙ በየወሩ ከኢንተርኔትና ከሌሎች አገልግሎቶቹ ከ2.3 ቢሊዬን ብር በላይ የሚሰበስብ ቢሆንም ለደንበኞቹ ተገቢውንና ጥራት የለው አገልግሎት አይሰጥም በሚል ስሙ በትችት ተደጋግሞ ይነሳል።

ኢትዬ ቴሌኮም የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በራሱ ምክንያት ቢያቁዋርጥ እንኩዋን ያለምንም ማካካሻ ገንዘቡን የሚሰበስብ ብቸኛ ቴሌፎን አቅራቢ ኩባንያ በመሆን እየሰራ ይገኛል።

ይህም ሆኖ ኢትዬ ቴሌኮም በአጭበርባሪዎች የገቢዬን 2በመቶ እያጣሁ ነው ሲል በኮርፕሬት በኩል እንዲህ ይላል

ኢትዬ ቴሌኮም ወደ ውጪ ሀገራት ለሚደረግ የእንድ ደቂቃ ጥሪ በአማካይ 12 ብር ሲያስከፍል አገልግሎቱን ከድርጅቱ ገዝተው ያለ ህጋዊ ፍቃድ በስውር የሚሰሩ የኢንተርኔት ካፌዎች ግን ለአንድ ደቂቃ ጥሪ የሚያስከፍሉት 2 ብር ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለድርጅቱ መጭበርበር ዋናው ምክንያት የራሱ ያልተገባ የዋጋ ንረት ነው ሲሉ ብዙዎች የሚናገሩት።

ብቸኛው ተቁዋም ኢትዬ ቴሌ ኮም ከሁለት አመት በፊት አዳዲስ የማስፋፊያ ስራዎችን ይፋ ቢያደርግም ማጠናቀቅ አልተቻለውም። ድርጅቱ ለማስፋፍያ ስራው 1.6 ቢሊዬን የአሜሪካን ዶላር ወጭ አድርጎ ስራው ያለመጠናቀቁን ምክንያት ሀላፊው ያብራራሉ።

የሚታለበው ላም ኢትዬ ቴሌ ኮም ከማስፋፍያ ስራው ጋር በተያያዙ ውሎች ምክንያት የሚሊዬን ዶላሮች መጭበርበር የሚፈጸምበት ተቁዋም መሆኑ በሰፊው ይነገራል።ከዚሁ ከጉቦ ቅሌት ጋር በተገናኜ የቀድሞ የተቁዋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ የአመታት የእስር ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ይታወሳል።