Home Current Affairs ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ

ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ

April 27, 2016 3
Share!
Major Dawit Giorgis

Major Dawit Giorgis

(ዋዜማ)- እንደ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ግምገማ ኢትዮዽያ ከመቼውም በላይ የፀጥታና ደህንነት አደጋ አንዣቦባታል፣ ይህን አደጋ በድል ከተሻገርነው ኢትዮዽያ በማያዳግም መልኩ ጠንካራ ሀገር ሆና ትወጣለች። የሳዑዲ አረቢያ የውሀቢ እስልምና ዘውግ የደቀነው አደጋ ከወዲሁ ሊታሰብበት የሚገባ ነው ባይ ናቸው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የጥናት ፅሁፍም አላቸው። አደጋዎቹን መገንዘብና መፍትሄዎቹ ላይ በርትቶ መረባረብ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያሰምሩበታል። ከኤርትራ ጋር ያለንን ግንኙነት በማሻሻል ለአደጋ ተጋላጭነታችንን መቀነስ ይቻላል ይላሉ የጥንቱ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ምሩቅና የጦር መኮንን የሆኑት ሻለቃ ዳዊት። በኢትዮዽያ በጦርነትና በሀይል የሚመጣ ለውጥ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ሊያመጣ ይሳነዋል ።ሻለቃ ዳዊት አሁንስ ምን እየሰሩ ነው? ሁሉንም ከራሳቸው አፍ ስሙት፣ ዋዜማን አድምጡ አጋሩ3 Comments

 1. ዜና ወልደማርያም። April 27, 2016 at 6:15 pm

  ሻለቃ ዳዊት
  የሰጠውን አስተያየት አዳመጥኩት።በመንግስት ስልጣን ላይ ሆኖ በዚህች አገር ላይ አደጋ ካመጡ ስዎች አንዱ ሻለቃ ዳዊት ነው።የትኛውም አመለካከቱ ዛሬ አልተለወጠም። ካሳ ከበደናዳዊት አንድ ዓይነት ነገር ይነግሩናል።ከኤርትራ ጋር በቶሎ አንድላይ ሆነን አደጋ እንከላከል የሚሉት “አደጋ” በስልጣን ላይ ሆነው ሲናገሩት የነበረ ተራውን ህዝብ የሚያስደነግጥ ምን ይሻለናል በሚል ጭንቀት ውስጥ የሚከት የገዥ ማስፈራርያ ነው።ምንድነው አንድ ሀገርን ከአደጋ ነፃ የሚያደርጋት ? ሻለቃ ዳዊት ሙሉ እድሜውን ሳይገባውናሳይሰራው ወደ ህይውቱ መጨረሻ ገብታል።
  ኤርትራናወያኔ አንድ ናቸው።ለምን ለኤርትራ/ሻቢያ እንደሚዘመርለትና አደጋ ተከላካይነት እንድተመረጠ ከስድ ንባብ ያለፈ አንድም ጉዳይ ሻ/ዳዊት አልተናገረም።እንድ ካሳ ከበድ ሁሉ።ኤርትራ ውስጥ ምን ዓይነት መንግስት እንዳለ እኔ ሳልሆን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሉትን እንካን ለምን ሳይጠቅስ እንዳለፈ ዳዊት እራሱ ችግር እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ።
  ሻለቃ ዳዊት ስለሀገር አንድነትም አውርታል።የሀገሪ አንድነት ምን እንደፈረስ አንድ መስመር አልተነፈሰም።ጋዜጠኛውም አልጠየቀውም።አደጋ ብቻ።አደጋ መከላከያና አንድነት ማስጠበቅያ ምንድነው ሻለቃ ዳዊት ? የኤርትራ መንግስት ነው ? ለምን ታዲያ ሻቢያን 30 ዓመታት ወጋህው ? የኢትዮጵያ አንድነት እስክ ተጠበቀ ድረስ ዛሬም ይላል።ገደብ ወይም ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል።የኢትዮጵያ ችግር መፍቻ ፤አደጋ መከላከያ ዳዊት ፣ካሳከበድ ኤርትራ ሳይሆኑ፤የኢትዮጵያ ህዝቦች ያላንዳች ገድብ ሀገራቸው ምን ዓይነት መሆን እንዳለባት በነፃነት ሲወስኑ ነው።ምን አማራጭ የሌለው መንገድ ይህ ነው።የእኔ ነው የምንለው መንግስት በነፃነት ሲኖረን ነው።ሻለቃ ዳዊት ነፃነት የሚለውን ሦስት መስመር አስምርበት።ሁሉም ሰው ይሞታል እውነት ተቀብሎ ቢሞት ይመረጣር።ሀገራችንን በእጅጉ በተወሳሰበ ችግር ውስጥ ከከተቱ ሰዎች አንዱ አንተነህ።ዛሬም ምንም መፍህቴ አላመጣህም።የሁሉም ችግር መከላከያ በነፃነት የሚቕቕም ዲሞክራሳዊ መንግስት ነው።የአንተ ምክር አንድም የሚረባ ነገር የለውም።የጥፋት ኃይሎች !!!
  ሁልጊዜ ሰላም ይሁን።
  አሜን።

  Reply
 2. Tola Dejene April 28, 2016 at 1:29 pm

  በሁሉም አሰተያየት ተስማምቻለሁ ከበአመፅ ከሚለው በቀር።የህ መንግሥት በሠላማዊ ብቻ በሚል ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል ።አሁንም ጥረቱ ቀጥሏል።ነገግን መሪዎቹን በማሠር ሕዝቡን ከመቀጥቀጥ በመግደል ይኸው አለ።የጠቀስካቸው ችግሮች መንሴው የዚህ መንግሦት ራሱን ሥልጣን ማቆየት ነው።አገር ሕዝብ የሚለው ጢቂት መሪዎቹን ማቆየት የሚል አላማ ብቻ ነው።ይህም በዘረኝነት ተደራጅቶ የሚገለን የሚያሰድደን በትጥቁና በደህንነቱ መረብ ነው።ስለዚህ በሰላም ብቻ በተደጋጋሚ ተሞክሯል አሁንም ይኼው ቀጥሏል።ነገር ግን ምንም ፍንጭ አላሰየም።ግድያው ቀጥሏል።ስለዚህ የትጥቅ ትግሉንም መጨመር አስፈላጊ ነው ።ዋናው ግልፅ ያለ አላማ ያለው የተደራጀ መሆን ይገባዋል እንጂ በሉም አቅጣጫ ይህን መንግሥት መታገል ተገቢ ነው ብዪ አምናለሁ።ደርግ የመጣው በሠላማዊ መንገድ ነበር ውጤቱ የምናውቀው ነው።ወያኔ በትጥቅ ነው።አሁን የምናየው ነው።ስለዚህ በሁሉም መንገድ መሄድ ይጠይቃል ።ዋናው በዲሞክራሲ ማመን።ቀጣይ የተፈራው የእርስ በርስ ግጭት እንዳይመጣ የተደራጀም የታጠቀ ኀይልም ያስፈልጋል ።በሌላም በኩል በሠላም፡ በአመፅም የሚያምኑ ሁሉ የዲሞክራሲ ዕምነት እስካለ ድረስ አብሮ የማይሠራበት አይታኝም ።የምንፈልገው ለማግኘትት መተባበር ፡መረደዳት ብሎም ግንባር መፍጠር ነው ።ዋናው ከዚህ መከራ ሕዝብን እናድን ነው።

  Reply

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Tweets by @Wazemaradio
Skip to toolbar