Home Talking points Benegerachin Lay-Discussion ስለምን የኦሮሞ ወገኖቼን ተቃውሞ ሳልቀላቀል ቀረሁ?

ስለምን የኦሮሞ ወገኖቼን ተቃውሞ ሳልቀላቀል ቀረሁ?

February 26, 2016 2
Share!
Young Oromo Protestors SM

Young Oromo Protestors SM

(ዋዜማ ራዲዮ) በሀገሪቱ ያለው ጭቆና ገፈት ቀማሽ የሆነው ሁሉም ኢትዮዽያዊ ሆኖ ሳለ ስለምን ሁሉም በጋራ ተቃውሞውን ማሰማት ተሳነው? የሚለው ጥያቄ የሚያናድድም የሚያስፈራም ድባብ አለው። በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ደም እየከፈለ ባለበት በዚህ ጊዜ አብሮ ለመቆም የሚሞክር የሌላ አካባቢ እንቅስቃሴ አለማየት ጉዳዩን በአፅንኦት እንድንመለከተው ግድ ይለናል። ዋዜማ ስለምን ሌላው ህዝብ ከኦሮሞ ወገኑ ጎን ለመቆም ተሳነው? ለሚለው ምላሽ ሊሆኑ የሚችሉ የመነሻ ሀሳቦችን ታነሳለች። ፕሮግራሙን አድምጣችሁ የናንተን ሀሳብ ደግሞ አጋሩን።2 Comments

 1. Fitih February 26, 2016 at 5:24 pm

  You have somehow analyzed that protests have their own dynamic and follow their internal logic but this does serve to explain almost anything, teleological. Mesfin has at the end come to the point and said that there is a trigger to the fire which can mean that for any underlying or smoldering resentment on the part of the people protests occur contingently, as in when a person put himself on fire in Tunisia or the Master Plan in Ethiopia.

  This leads one to say that the lack of similar protests in other parts of Ethiopia have not met their own triggering or contingent variable. Adding also that the Oromo question is also different in its underlying logic of lack of democracy or freedom in general.The fact that what was cried out in one part of Oromia against a master plan has traveled so much a distance and traversed other ‘people’ and echoed in other Oromo areas will once again show the strength of identity politics that some politicians try to defy and still claim they will build a new democracy of citizenship and not identity.

  It might serve the conversation to always keep in mind that for TPLF any opposition by Oromos is the most unwelcome and this is why too many Oromos are in prison compared to others. Unwelcome because what TPLF has built as a new regime of multi ethnic politics for the best part rests on the the repressed ethnic history or the Oromo and other ethnic groups in the South. Oromo being bigger in size and being one among the few in pioneering ethno nationalist movements of the likes of ELF or ONLF or TPLF, what EPRDF has proclaimed to have erased, ethnic domination, largely borrows its wailing from the cry of the Oromo people. Then what more is unnerving for the TPLF than hearing the criesof the same people over whose pain and anguish it has built its throne. As for the Amhara any protest is seen as a latent dose of aggression. But most of all, since TPLF knows the force of ethnic movements that appeal to the most natural, primordial as some say, and its instrumental success as opposed to mere appeals to lack of democracy or civic rights, the Oromo opposition or any other opposition appealing to ethnicity is the most threatening for the regime.

  Reply
 2. ቢንያም (The Fugitive) February 26, 2016 at 7:24 pm

  “በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?” አሞ 3: 3
  የተወደዳችሁ የዋዜማ ሬድዮ ደራሲዎች እንደምን አላችሁ? በያላችሁበት አገር እና አካባቢ ሰላማችሁ እና ጥበቃችሁ ይብዛ:: የዋዜማ ሬድዮን መመስረት ሳስብ ሁል ግዜ ሀሴት አደርጋለሁ በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ ሀገሮች ሳትፈልጉ በግድ ከቀዬአችሁ ተሰዳችሁ (The Fugitive) በባእድ ሀገር በስደት ከያላችሁበት ተሰባስባችሁ ያላችሁበት የስደት አገር ሁናቴ እና ግዜ ሳይገድባችሁ እንዲሁም ግዜን ዋጅታችሁ ይህችን “ዋዜማ” ድምጽን የኣእምሮአችንን እና የልባችንን የነጻነት ሀሳቦቻችንን እንድንተነፍስበት ስላቋቋሟችሁልን በዚሁ አጋጣሚ በእግዚያብሔር ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
  በዛሬው የዋዜማ ሬድዮ ፕሮግራም ዋና አብይ አርእስት ሆኖ የተነሳው ከአራት ወር በላይ ባስቆጠረው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በሞከሩት ሰላማዊ ሰዎች ላይ በትረ ዙፋኑን በተቆናጠጠው የህውሀት መንግስት ትእዛዝ እነዚህ ንጹሀን የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ከህጻን እስከ አረጋውያን ድረስ በእኩለ ቀን በግፍ ተጨፍጭፈዋል:: በመጨፍጨፍም ላይ ናቸው:: ወደፊትም ጭፍጨፋው እንደሚቀጥል የህውሀቱ ጃንደረባ አቶ ሀይለማርያም በግልጽ በድምጽ ማጉያቸው ተናግረውናል:: ይህንን ካልኩ ዘንዳ ዛሬ በተነሳው ርእስ ጉዳይ ላይ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የራሴ የሆኑ ሀሳቦች አሉኝ ስለሆነም ከፈቀዳችሁልኝ እኔም ሀሳቤን በአስተያየት መልክእንደሚከተለው አቀርባለሁ::
   መስፍኔ ከተናገረው የሀሳበ መልስ ላይ መሰረት በማድረግ አሁን የተከሰተው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች ጥያቄያቸው የ “ዲሞክራሲ” ጥያቄ ነው ተብሎ የነበረ ሲሆን እኔ ይህንን አባባል አልጋራውም:: ምክንያቱም “ዲሞክራሲ” በተፈጥሮው ሶስተኛው እና የመጨረሻው እረድፍ የሚፈረጅ እና ፍሬው ለሁሉም የሚታይ ነው ብዬ ነው የማምነው:: እኛ የኦሮምኛ ሆኑ ሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪ ኢትዮጵያ ህዝቦች በመጀመሪያ ደረጃ የሚያስፈልገን “ነጻነት” (liberty) በሁለተኛ ደረጃ የሚያስፈልገን “ፍትህ ”(Liberalism) በሶስተኛ ደረጃ እና በመጨረሻው የሚያስፈልገን ደግሞ “ዲሞክራሲ” ነው:: ስለሆነም አሁን አብዛኞቻችን አንድ ወጥ ፓለቲካዊ አስተሳሰብ (ሞኒዝም) ተተብትበን እና አንድ አይነት ቋንቋ እያወራን ከፈረሱ የጋሪውን ጎማ አስቀድመነዋል:: ስለሆነም በመጀመሪያ ወደ ፈረሱ “ነጻነት” (liberty) እንመለስ ሲቀጥል ወደ ጋሪው “ፍትህ ”(Liberalism) በሶስተኛው እና የመጨረሻው ወደሆነው ወደ ጋሪው ጎማ ደግሞ “ዲሞክራሲ” እንመለስ ስለዚህ ወደ መጀመሪያው ጥያቄ ስንመለስ ያኔ ምክኒያታዊ መፍትሄዎችን እናገኛለን:: ምክንያቱም ዲሞክራሲ ብቻውን ቢተገበር እንኳ በራሱ በቂ እና ሙሉ መሆን ስለማይችል::
   ከአራት ወር በላይ ባስቆጠረው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች “እምቢኝ አሻፈረኝ” ለማለታቸው ዋናው ምክንያት ሆኖ የቀረበው ከአዲስ አበባ ከሚከለሰው የማስተር ፕላን ፕሮግራም ባሻገር የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች “ንቃተ ህሊናው” አድጓል:: ይህ አነጋገር በተቃራኒው በሌላ ቋንቋ አማርኛ፣የደቡቡ፣የሱማሌው፣የአፋሩ፣የጋምቤላው …..ወዘተረፈ ቋንቋ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ “ንቃተ ህሊናው” ኮስምኗል ማለት ነው? እዚህ ላይ እኔ “ንቃተ ህሊና” አድጓል በሚለው ላይ አልስማማም:: ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በዚሁ በዋዜማ ሬድዮ በቀረበው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች “እምቢኝ አሻፈረኝ” ህዝባዊ አመጽ ላይ “አመጹን መንግስት ለፓለቲካው አላማ ፍጆታ ያውለዋል” ተብሎ ተነስቶ የነበረ ሲሆን እኔም ይህን ሀሳብ እጋራለው እንዲሁም “አመጹን ሆነ ብለው ያስነሱት የኦህዴድ ባለስልጣኖች ናቸው ምክንያቱም ዋናው እና ትልቁ ጥቅማቸው ስለተነካ” የሚለውንም መላምት በከፊል እጋራዋለው እኔ በግሌ የሚታየኝ የረሀቡ ጠኔ እና የኑሮ ውድነቱ ከመቼውም ግዜ በላይ ያንገሸገሸው የሀገሬ ኢትዮጵያ ህዝብ ከሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ግንባር ቀደም ሆኖ “እምቢኝ አሻፈረኝ” ብሎ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ ደረቱን እና ግንባሩን ለግፈኞች ጥይት እንደሰጠ እረዳለሁ::
  ለምንድ ነው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች “እምቢኝ አሻፈረኝ” ህዝባዊ አመጽ ላይ ሌሎች ኢትዮጵያኖች የማይሳተፉት ለሚለው ጥያቄ መስፍኔ ጥሩ አድርጎ አብራርቶታል:: እኔ የምጨምረው መስፍኔ እንዳለው እጅግ መራራው ዘር በተዘራ ከ24 አመት ቡኋላ ለመብል ደርሶ መራራውን ዘር የተከለው የተክሉ ባለቤት “ህውሀት” ብቻ ጣፍጦት ሲበላ ሌሎቻችን ሁሉ ግን ከሀሞት ይልቅ እጅግ መሮናል:: ስለሆነም ወንድሞቻችን እና የገዛ ስጋችን ከሆኑት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያኖች ጋር እንደቀድሞው ግዜ አንድ ለመሆንና አብሮ ለመጓዝ ሳናውቀው መስሎን በዲሞክራሲ ስም በምእራብያኖቹ እና በ“ህውሀት” ተመርዞ የተሰጠንን እና የበላነውን መጥፎ የዘር መርዝ ፍሬ ለማርከስ እውነተኛ የሆነውን ወተት በመጣጣት አስታውከን ስናስወጣ ብቻ ነው አብሮ መጓዝ የሚቻለው:: ይህ ማርከሻ ወተት ደግሞ ልዩነትን እና ቅራኔዎችን እንዲሁም አለመግባባቶችን በግልጽ በመነጋገር ወደ ብሄራዊ መግባባት እርቅ ሲመጣ ብቻ ነው ትብብራዊ አንድነት ማድረግ የሚቻለው:: ሌላው ይህንን ክፉውን እውነተኛውን የዘር መርዝ ፍሬ እስከአሁን ድረስ ቀምመው በየሄድንበት የሚግቱን ምእራባዊያኖቹ የሰብአዊያን መብት ተቆርቋሪ አገሮች ዋና ደራሲያኖቹ ናቸው:: እዚህ አውሮፓ ስደተኝነት ጥያቄዎትን ለመቀበል አንዱ እና ዋናው የኦሮምኛ እና የኢትዮጵያ ሱማሌ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑ የስደኝነት ጥያቄዎ በአፋጣኝ አዎንታዊ መልስ ያስገኝሎታል:: ከሰሞኑ የአውሮፓ ህብረት ባወጣው በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፓርት ላይ “አማራ” እና “ትግሬ” የኢትዮጵያ ኦሮሞ እና ሱማሌ ህዝብ ላይ እስከዛሬ ድረስ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል የሚል ሪፓርት አውጥተዋል:: ይህ ማለት እንደሚባለው ተረቱ “ ሊበሏት ያሰቧትን ዶሮ ጅግራ ይሏታል” መሆኑ ነው የአውሮፓ ፓርላማ ሪፓርት ስለሆነም ከላይ ለመግቢያ ከተዋስኩት የታላቁ መጽሐፍ ቃል የአምላካችን የእግዚያብሔርን ቃል ለዚህ ጽሁፍ ሀሳብ ትክክለኛ ገላጭ ነው ብዬ ስላሰብኩ ቃሉን በድጋሚ በመድገም ለዛሬ እሰናበታችኋለሁ:: “በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?” አሞ 3: 3
  ቸር እንሰንብት!
  ቸር ወሬ ያሰማን!
  ቢንያም (The Fugitive)

  Reply

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Tweets by @Wazemaradio