Category: Current Affairs

የአዲስ አበባ አስተዳደር በጋራ መኖሪያና በንግድ ቤቶች ላይ ጥሎት የነበረውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ህትመት እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ

ዋዜማ ራዲዮ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎት ላይ ጥሎት ከነበረው እገዳ መካከል፣ በኮንዶሚኒየም እና ንግድ ቤቶች ላይ የጣለውን የይዞታ ካርታ ህትመት እገዳን በማንሳት አገልግሎት እንዲጀመር አዘዘ።…

የኢትዮጵያ መንግስት የድሕረ ጦርነት የፀጥታና ደህንነት ስጋቶች ላይ እየመከረ ነው

[ዋዜማ ራዲዮ]- የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ሲካሄድ የነበረው ጦርነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል መጠናቀቁን ካወጀ በኋላ በድሕረ ጦርነቱ በሚኖሩ የፀጥታ ስጋቶች ላይ ምክክር ማድረግ መጀመሩን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ማረጋገጥ ችላለች።…

በውጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሀገር በብዛት መግባታቸውን ተከትሎ የጥቁር ገበያ የምንዛሪ ተመን አሸቆልቆሏል

ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ መንግስት በውጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን የገና እና የጥምቀት በዓላትን በሀገር ቤት በመገኘት እንዲያከብሩ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በርካታ እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ይገኛሉ። ይህን ተከትሎ…

ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ግድያ፣ ማፈናቀልና የጋዜጠኞች እስራት ትኩረት ይሰጠው ሲል ኢሰመጉ ጠየቀ

ዋዜማ ራዲዮ- በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ግድያ፣ ማፈናቀልና እስራት ትኩረት እንዲሰጠው እንዲሁም በተለያዩ ምክንያች እየታሰሩ የሚገኙ ጋዜጠኞች በአፋጣኝፍትህ የማግኘት መብታቸው እንዲጠብቀላቸው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ…

ኢሰመጉ በማይካድራ ፣ ሁመራ እና ዳንሻ ከ 1,100 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን የሚያሳይ ጥናት ይፋ አደረገ

ዋዜማ ራዲዮ-በጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ፣ ሁመራ፣ አብደራፊ፣ አብርሃጅራ እና ዳንሻ ከተሞች እጅግ የከፉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸሙንና ህጻናትን ጨምሮ 1,100 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ…

የኢትዮጵያ መንግስት በ100 ቢሊየን ብር ካፒታል የኢንቨስትመንት ግሩፕ አቋቋመ

ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ከተቋቋሙ በካፒታል አቅም ግዝፈታቸው ከቀዳሚዎቹ የሚመደብ የመንግስት የልማት ማስፋፊያ (የኢንቨስትመንት ግሩፕ) አቋቋመ። ተቋሙ “የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ግሩፕ” የሚሰኝ ሲሆን የመቋቋሚያ ካፒታሉም 100 ቢሊየን ብር መሆኑን…

ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ዋዜማ ራዲዮ- ላለፉት ሰላሳ አመታት በኢትዮጵያ የስነፅሁፍ ዘርፍ ስመጥር የነበረውና በአወዛጋቢ ፅሁፎቹ የሚታወቀው ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ዋዜማ ከቅርብ ቤተሰቦቹ ስምታለች። ተስፋዬ ያለፉትን ወራት በፅኑ ታሞ…

በድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዝ የተከሰሰችው ላምሮት ከማል 3 ወር እስራት ተበየነባት

ዋዜማ ራዲዮ- ከድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዝ በትላንትናው እለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ተኛ የፀረ ሽብር እና የህገ-መንግስት ጉዳዩች ችሎት ቀርባ በተከሰሰችበት አንቀፅ ጥፋተኛ የተባለችው ላምሮት ከማል…

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረጥና ታሪፍ ነፃ መብት (አጎዋ) ታገደች

ዋዜማ ራዲዮ- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሐሙስ ምሽት ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት የአፍሪቃ ሀገራትን Africa Growth Opportunity Act (Agoa) የቀረጥና ታሪፍ ነፃ መብት መሰረዛቸውን ይፋ አድርገዋል። ኢትዮጵያ በትግራዩ ጦርነት ሳቢያ ከንግድ…

በጦርነቱ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የ34 ቢሊየን ብር የመልሶ ማቋቋም መነሻ ድጋፍ እየተዘጋጀ ነው

በሁለት ወራት ውስጥ መንግስት በመልሶ ግንባታ ላይ ያተኮረ አዲስ በጀት አዘጋጅቶ ያቀርባል ዋዜማ ራዲዮ- በመንግስትና በሕወሓት አማፅያን መካከል ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ጦርነት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚረዳ የመጀመሪያ ዙር…