Author: wazemaradio

“በአማራ ክልል ከህግና ፍርድ ውጪ የሚፈፀመው ግድያ እና እስራት አሳሳቢ ሆኗል” ኢሰመኮ

ዋዜማ– የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎችና የዘፈቀደ እስሮች “እጅግ አሳሳቢ” ኾነዋል ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢሰመኮ፣…

ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚዛወሩ የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ግዴታ ተጣለባቸው

ዋዜማ– በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ክልላዊ የ6ኛ ክፍል መመዘኛ ፈተና መጀመሩን ተከትሎ የ7ኛ ክፍል ተመዝጋቢ ተማሪዎች፣ ወደ አዲስ አበባ ለመዛወር የመመዘኛ ፈተና የመውሰድ ግዴታ እንደተጣለባቸው ዋዜማ ተረድታለች፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ…

በአማራ ክልል የከተማ መሬት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ታገደ

ዋዜማ- የአማራ ክልል መንግሥት በሁሉም የክልሉ ከተሞች ሁሉንም አይነት የከተማ መሬት አገልግሎቶች ማገዱን ዋዜማ ተረድታለች። የክልሉ መንግሥት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የክልሉ ከተሞች የከተማ መሬት ማስተላለፍ፣ ማዘጋጀትና አገልግሎት መስጠት ሥራዎች ሙሉ…

የጥሬ ገንዘብ እጥረት ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች ገንዘባቸውን እንዲከዝኑ እያስገደደ ነው

ዋዜማ- የግል ንግድ ባንኮች የገጠማቸው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ቀጥሎ ለደንበኞቻቸው መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ዋዜማ ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል። የጥሬ ገንዘብ ዕጥረቱን ተከትሎ፣ ባለሀብቶችና ነጋዴዎች ጥሬ…

ኢሰመኮ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙ እስረኞች አያያዝ ጉዳይ ላይ ጥብቅ ክትትል አንዲደረግ አሳሰበ

ዋዜማ- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ አፈጻጸም ጋር በተገናኘ በቁጥርጥር ስር ውለው በአዋሽ አርባ ወታደራዊ እዝ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ እስረኞች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እንዲደረግ አሳሰበ፡፡…

ቻይና ግማሽ ቢሊየን ዶላር የኢትዮጵያን ዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘመች

ዋዜማ- የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ፣ ቻይና ፣ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 2024 ድረስ መክፈል የሚጠበቅባትን ግማሽ ቢሊየን ዶላር የኢትዮጵያን ዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘመች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ አባልነቷ ተቀባይነት ባገኘበት የደቡብ…

ሀገር አቀፍ ደመወዝ ወለልን ለመወሰን የሚያስችለው ቦርድ እንዲቋቋም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተስማሙ

ዋዜማ- የሰራተኛ ማህበራት መሪዎች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን የሚያስችል የደሞዝ ቦርድ እንዲቋቋም መስማማታቸውን ዋዜማ ተረድታለች። የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈደሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ…

የህዳሴ ግድብ ድርድር: ከአፍሪቃ ህብረት ወደ ተባበሩት አረብ ዔምሬትስ?

ዋዜማ- የህዳሴውን ግድብ “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ” ዕልባት ይሰጣል የሚል ተስፋ የተጣለበት ድርድር በካይሮ እየተካሄደ ነው።ድርድሩ በተባበሩት አረብ ዔምሬትስ አደራዳሪነት የተጀመረው ጥረት የመጨረሻ ምዕራፍ ነው። በአፍሪቃ ህብረት የተጀመረው ጥረት ቀጣይነት ጥያቄ…

ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ባንኮች የማበደሪያ ወለድ መጠናቸውን ለመከለስ እየተሰናዱ ነው

ዋዜማ- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ለገደብ  ከቀናት በፊት አዲስ የገንዘብ ማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የንግድ ባንኮች የማበደሪያ ወለድ መጠናቸውን ለመከለስ እየተሰናዱ  መሆኑን ዋዜማ ስምታለች። የማበደሪያ ወለድ መጠን መጨመር…

በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች የመንግሥት ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ታገደ

Photo- Amhara regional government ዋዜማ- የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የመንግስት ተቋማት ገንዘብ አንዳይንቀሳቀስ ማገዱን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ለመረዳት ችላለች። የአስቸኴይ ጊዜ ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ ለቀናት የተጣለው አጠቃላይ…