Samora
Samora Yenus /FILE

ዋዜማ ራዲዮ- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈጻሚ ኮማንድ ፖስት በርካታ ድንጋጌዎችንአውጥቷል፡፡ መመሪያውግንበህግ ባለሙያ የተዘጋጀ አይመስልም፡፡ ቋንቋውም ግልጽ አይደለም፡፡በጥድፊያ የተረቀቀ እና ግልጽነት የጎደላቸው በርካታ ጥቅል አንቀጾችን ያካተተ ነው፡፡ መመሪያው በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ የተደነገጉ ወንጀሎችን ከአዳዲስ ክልከላዎች ጋር ደባልቆ ነውየደነገገው፡፡በይዘቱ ግንዴሞክራሲያዊ መብቶችን ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰብዓዊ መብቶችንምየሚደፈጥጥ መመሪያ ሆኗል፡፡

ቻላቸው ታደሰ የዚህ አዋጅ ገደብ የለሽ የመብት ድፍጠጣ ከተነገረንም በላይ የከፋ መሆኑን ያብራራል። ዘገባውን በድምፅ ይከታተሉት አልያም ንባብዎን ይቀጥሉ።

በ1967ዓ.ም ጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ካወጣው አፋኝ አዋጅ ወዲህ በሀገሪቱ እንዲህ ዓይነት እጅግ አፋኝ መመሪያ ሲወጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ የያኔው የደርግ አዋጅ ቢያንስበቋንቋ ግልጽነቱ እና በተፈጻሚነት ወሰኑ ካሁኑ መመሪያ የተሻለ እንደነበር መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ሀገሪቱ ያኔየነበረችበት አስቸጋሪሁኔታም ቢሆንካሁኑ የባሰ መሆኑ አይካድም፡፡ያሁኑ መመሪያ በአፋኝነቱ ሀገሪቱ ገጥሟታል ከሚባለው ቀውስ ጋር ፈጽሞ አይመጣጠንም፡፡ በተለይ መንግስት ያለ የሌለ የጸጥታ ሃይሉን በመላ ሀገሪቱ ባሰማራበት ሁኔታ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ አስገራሚ ሆኗል፡፡

ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ይህን ከባድ መመሪያ ያወጣው ለተቀሰቀሱበት ህዝባዊ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በሰጠው ሃይል የተቀላቀለበት ምላሽ ላይ ዓለም ዓቀፍ ውግዘቶች እና ትችቶችእየከረሩ መሄዳቸውን ከተገነዘበ በኋለ ነው፡፡በመመሪያውከግለሰቦች ሲቪል ህይወት እስከ መንፈሳዊ ህይወት፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እስከ እምነት ተቋማት፣ ከውጭ መገናኛ ብዙሃን እስከውጭ ዲፕሎማቶች፣ ከመሃል ሀገር እስከ ጠረፍ ድረስ ያልተከለከለ ድርጊት ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በመሆኑም በፖለቲካ እና ጸጥታ ረገድ ብቻ ሳይሆን በዜጎች የዕለትተለት ህይወት ላይየሚኖረው አሉታዊ አንድምታ የትየለሌ ነው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ኦሮሞ ሜዲያ ኔትወርክ የመሳሰሉ በውጭ ሀገር የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ከመቼ ጀምሮ በሽብርተኝነት እንደተፈረጁ ባይታወቅም በመመሪያው ግንእነዚህን መገናኛ ብዙሃን መከታተል እና ግንኙነት ማድረግ በወንጀልነት ተደንግጓል፡፡ ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ኢሳትን ከግንቦት ሰባት ጋር፣ የኦሮሞ ሜዲያ ኔትወርክን ደሞ ከኦሮሞ ነጸነት ግንበር ጋር በማያያዝ በተለምዶ በሽብርተኛነት ይፈርጃቸዋል እንጂ በህግ ግን በይፋ በሽብርተንነት የተፈረጁበት ጊዜ የለም፡፡

የኮማንድ ፖስቱ መመሪያ ግን በኢሳት እና ኦሮሞ ሜዲያ ኔትወርክን መመልከት ላይ እገዳ በመጣል አልተገታም፡፡ ይልቁንስ ኢሳት፣ ኦሜን እና የመሳሰሉ የሚል ሃረግ መጠቀሙ ሌሎች በውጭሀገር የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንንም ሊያካትት እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡ የመሳሰሉት የሚለው አገላለጽ ቪኦኤን እና የጀርመን ድምጽን ጨምሮ ሌሎች በውጭ በሚኖሩኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የሚዘጋጁ የሬዲዮ ስርጭቶችን ለማካተት ታስቦ ሊሆን ይችላል፡፡የአንቀጹ የክልከላ ወሰን እስከምን ድረስ እንደሚዘልቅ መረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡ በመመሪያውእንዲህ ዓይነት አገላለጽ መካተቱ ምናልባትም ሆን ተብሎ ዜጎች በተከለከለውና ባልተከለከለው ጉዳይ ላይ ግርታ እንዲፈጠርባቸው ለማድረግ ታስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ መመሪያው ግልጽነት የጎደለው ነው ለማለት የሚያስችለው አንዱ ባህሪውም ይኸው ነው፡፡

በጥቅሉ ሲታይ መመሪያው ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ውጭ ያሉ ሌሎች መገናኛ ብዙሃንን መከታተልን ወይም የጽሁፍ እና የቃል ግንኙነት ማድረግን ሙሉ በሙሉ መከልከሉ ብቻ ሳይሆንበቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሃሳቦች በማህበራዊ ሜዲያ ጭምር በመግለጽ መብት ላይ ሙሉ በሙሉ ገደብ መጣሉ ግልጽ ሆኗል፡፡ሀገር ውስጥ ያሉ የግል መገናኛብዙሃንም ስለ መመሪያው አፈጻጸም ጉድለት፣ ስለ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ወይም ወደፊት ስለሚቀሰቀሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች አንዳች ነገር ቢዘግቡ የመዘጋት ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑንእንዲያውቁት ተደርጓል፡፡

መመሪያውየኢኮኖሚአውታሮች፣የኢንቨስትመንትተቋማት፣የእርሻልማቶች፣ፋብሪካዎች እናመሰረተ ልማቶችባሉባቸው አካባቢዎችከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት እስከ ንጋቱ አስራ ሁለትሰዓት ድረስ መንቀቀሳቀስ ከልክሏል፡፡ የኢኮኖሚ አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች የሚባሉት ግን የትኞቹ እንደሆኑ ለማወቅ አይቻልም፡፡ ዜጎች ከመሰረተ ልማቶቹ በምን ያህል ርቀትመገኘት እንዳለባቸውም ግልጽ አይደለም፡፡ በተለይ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ መኖሪያቸው አቃቂ እና ቃሊቲ የሆነ የመንግስትም ሆኑ የግል ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው ምሽት አስራ አንድሰዓት ተኩል ወጥተው ወደ ቤታቸው ለመሄድ መቸገራቸው አይቀርም፡፡ በጥቅሉ ሲታይ መመሪያው ሰዓት እላፊው በየትኛውም ቦታ እንዲከበርለት የፈለገ አስመስሎታል፡፡

ብዙዎቹ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዲሱ ዓመት ተማሪ መቀበያ ጊዜያቸውን ሲያራሳዝሙ የሰነበቱት የአሁኑ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ መሆኑ አሁን ግልጽ ሆኗል፡፡ ባሁኑ መመሪያየሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት ጨምሮ ሁሉም የጸጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ገብተው አድማ በሚያነሱ አካላት ላይ የሃይል ርምጃየመውሰድ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሌላው አስገራሚው የመመሪያው አንቀጽ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ እና ከጸረ-ሰላም ቡድኖች ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግን መከልከሉ ነው፡፡ መመሪያው ጸረ-ሰላም ሃይሎች በማለትየፈረጃቸው አካላት እነማን እንደሆኑ በስም ተዘርዝረው አልተቀመጡም፡፡ መንግስት እንዲህ ዓይነቱን ጥቅል አገላለጽ ሲጠቀም የመጀመሪያው ባይሆንም ካሁኑ በህግ ከሚያስቀጣው ጥብቅመመሪያ አንጻር ሲታይ ግን ስያሜው መንግስትን ክፉኛ የሚተቹ ዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶችንም ሊያካትት እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ባጭሩ ዜጎች በውዥንብር እናፍርሃት ቆፈን ተውጠው ከማናቸውም የውጭ አካላት ጋር ማንኛውንም ግንኙነት እንዳያደርጉ ታስቦ የተካተተ ድንጋጌ ይመስላል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሌላ አንቀጽ ደሞ ማንኛውምግልሰብከውጭመንግስታትምሆነከውጭመንግስታዊያልሆኑድርጅቶችጋርየሀገርሉአላዊነት፣ ደህንነትእናህገመንግስታዊስርዓትንሊጎዳየሚችልግንኙነትእናየመልዕክትልውውጥበማድረግላ ላይ ክልከላ ማስቀመጡ እነዚህን ድርጅቶች ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ነው፡፡ በተለይብሄራዊ ደህንነት እና ህገ መንግስታዊ ስርዓት የሚሉት አገላለጾች ደሞ ምንጊዜም ሽፍንፍን ያሉ እና ለተለጠጠ ትርጓሜ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ስለሆነም መንግስት ማንኛውንም የውጭ ግንኙነት በመዝጋት፣ ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ ከዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብ አለያይቶ የፈለገውን ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ግልጽ አድርጓል፡፡

የዚህ ድንጋጌ አንድምታ የሚያሳየው የየትኛውም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ከአውሮፓ ህብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ከምዕራባዊያን መንግስታት እናምናልባትም አዲስ አበባ ከሚገኙ ጋር የውጭ ዲፕሎማቶች ጋር የሀገሪቱን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ቀውስ እና መጻዒ ሁኔታ አስመልክቶ ማናቸውም ዓይነት ግንኙነት ማድረግ እንደማይችል ነው፡፡ ሰላም እናፀጥታሊያደፈርሱይችላሉተብለውየሚጠረጠሩሰዎችወይምቡድኖችወደተወሰነአካባቢወይምህንፃእንዳይገቡመከልከሉ ደሞ የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎችንከማናቸውም እንቅስቃሴ ለመገደብ መፈለጉን ያሳያል፡፡

ተቃዋሚ ድርጅቶች ላለፉት በርካታ ወራት መንግስት በህዝብ ላይ ሲወስድ የከረመውን የሃይል ርምጃ ብቻ ሳይሆን በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ማንነት እና ቁጥር ጭምር ለዓለም ዓቀፉህብረተሰብ እያጋለጡ እንቅልፍ ነስተውት ነበር፡፡ ያሁኑ መመሪያ ግን መንግስት እንደ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችንሙሉ በሙሉ እንዲያፍን ያስችለዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ተቃዋሚ ድርጅቶች ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት የሃይል ርምጃውን እንዲገታ ወይም ለአስቸኳይ ፖለቲካዊ ለድርድር እንዲቀመጥ ግፊት የሚያደርጉበት ዕድል ከሞላ ጎደል የተዘጋ ይመስላል፡፡ባጭሩ መመሪያው የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቋቋሙለትን ዋነኛ ዓላማ ዋጋ ቢስ አድርጎታል፡፡ ከዚህ በኋላ ፖለቲከኞችም ሆኑ ተራ ግልሰቦች በራሳቸው ላይ ካልፈረዱ በስተቀር የትኛውም መረጃ ወደ ውጭ ሊወጣ የሚችልበትን ዕድል መመሪያው ጥርቅም አድርጎ ተዘግቷል፡፡

አስደንጋጩ መመሪያ ምሽት ላይ በቴሌቪዥን ከመገለጹ በፊት ቀን ላይ የኢትዮጵያ ህገ መንግስታዊ ስርዓት ከየት ወዴት? በሚል አጀንዳ ላይ ኢህአዴግ ከታዋቂ ግልሰቦች፣ ምሁራን እናተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች ጋር ፓናል ውይይት አድርጓል፡፡ ይህንኑም በቴሌቪዥን ስርጭቱ አስተላልፏል፡፡ በዚህም ኢህአዴግ ማስተላፍ የፈለገው መልዕክት ከእንግዲህ ማንኛውንም ውይይትበራሱ አጀንዳ ቀራጭነት እና በራሱ ሜዳ ላይ ብቻ ለማካሄድ መወሰኑን ነው፡፡

መመሪያው ከስራ ገበታ መቅረትን፣ ንግድ መደብሮችን እና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን መዝጋት ህገ ወጥ ድረጊት ማድረጉ በተለይ በባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ ማነጣጠሩንያሳያል፡፡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተደነገገ ማግስት በተለይ በባህር ዳር ከተማ የግል ንግድ መደብሮች ዝግ ሆነው መቆየታቸው መንግስትን ሳያበሳጨው አልቀረም፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ግን እንዲህዓይነቱን ድርጊት ከዚህ በኋላ የማይታሰብ አድርጎታል፡፡

ህዝባዊእናብሄራዊበዓላትንማወክንአስመልክቶበመመሪያውየሰፈረውድንጋጌ በበኩሉ መንግስት መጭዎቹ የብሄር ብሄረሰቦች በዓል እና ጥምቀት በዓል በአደባባይ እንዲከበሩ መፈለጉንጠቋሚ ነው፡፡ ይህን በማድረግ ህግ እና ስርዓትን ባግባቡ ማስከበር መቻሉን ለማሳየት ይረዳዋል፡፡

መመሪያው በሃይማኖት ተቋማት ስጋት የሚፈጥሩ ስብከቶችን የመከልከል እና መቆጣጠር ስልጣን ለኮማንድ ፖስቱ ቢሰጥም ስጋት የሚፈጥር ስብከት የሚለው አገላለጽ ግን በጣም ጥቅልእና ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም፡፡ ስለሆነም የመመሪያው ዓላማ የዕምነት ተቋማት በመንግስት ፍቃድ ካላገኙ ወይም ካልታዘዙ በስተቀር በሀገሪቱተጨባጭ ሁኔታ ላይ አንዳችም ቃል ትንፍሽ እንዳይሉ ለማስፈራራት መታሰቡን ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል፡፡ ምናልባትም ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመንግስት የሃይልርምጃ ላይ የሰላ ትችቷን አቅርባ፣ ሀገር ዓቀፍ የሰላም ጥሪ ማድረጓ ኢህአዴግን ሳያስከፋው እንዳልቀረ መገመት ይቻላል፡፡

የመመሪያው ሌላኛው ዓላማ ትጥቅ ማስፈታት ይመስላል፡፡ በተለይ ኮማንድ ፖስቱ ወደፊት በሚለያቸው ቦታዎች ጦር መሳሪያ ከቤት ውጭ ይዞ መታየትን መከልከሉ በሀገሪቱ በተለይምበገጠራማ ቦታዎች ትጥቅ ለማስፈታት መወሰኑን ሊጠቁም ይችላል፡፡ ምንም እንኳ የተረጋገጠ መረጃ ባይገኝም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገ ወዲህ ግን በጎንደር አካባቢ ባላገሩን ትጥቅየማስፈታት እንቅስቀሰሴ መጀመሩ ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ያሁኑ መመሪያ ግን ዜጎች ህይወታቸውን እና ንብረታቸውን የመጠበቅ መብታቸውን ከሞላ ጎደል በመግፈፍ፣ በጸጥታ ሃይሎች ጠንካራክንድ ውስጥ እንዲወድቁ የሚያደርግ ሆኗል፡፡

ከሀገሪቱ ዓለም ዓቀፍ ድንበር ሃምሳ ኪሎ ሜትር ገባ ብለው በሚገኙ ቦታዎችን በሙሉ በአደጋ ቀጠናነት መፈረጃቸው የውጭ ጠላት ሴራ ተጠንስሶብኛል የሚለውን የመንግስት ትርክትየሚያጠናክር ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ማንኛውም ዜጋበነዚህየአደጋ ቀጠናዎችጦርመሳሪያይዞመንቀሳቀስ አይፈቀድለትም፡፡ መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱን በመላ የሀገሪቱ ጠረፍበማሰማራት ጠረፋማ ቦታዎችን በሙሉ በወታደራዊ ቀጠናነት መከለሉ ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባም ሆነ ከውስጥ የሚወጣ ጦር መሳሪያ እንዳይኖር ለማድረግ ያስችለዋል፡፡ ከዚሁ ጋርበተያያዘ ምንም እንኳ ስደተኞችን አስመልክቶ በመመሪያው የተደነገገው አንቀጽ ግልጽነት ቢጎለውም ማንኛውም ስደተኛ ያለ ቪዛ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለ ይመስላል፡፡ እነዚህሁለቱ ድንጋጌዎች ተደምረው መንግስት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሀገሪቱን ድንበር መዝጋቱን የሚያሳዩ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በዚህ ድንጋጌ በተለይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ክፉኛተጠቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቋሚ ነው፡፡

ባለፈው አንድ ዓመት በአመጽ የተሳተፉ ሰዎች ሁሉ በራሳቸው ፍቃድ በ10ቀናት ውስጥ እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ ማዘዙ ደሞ ከ10ቀናት በኋላ በጥቆማ እና በጥርጣሬ ጅምላ አፈሳ እናእስር ለመጀመር መዘጋጀቱን ጠቋሚ ሆኗል፡፡

አሁን ጥያቄው መንግስት እንዲህ ዓይነቱን በከባድ ክልከላዎች የታጀበ መመሪያ እንዴት አድርጎ ሊተገብረው ነው የሚለው ነው፡፡ መንግስት ያለ የሌለ ሙዓለ ንዋይ በማፍሰስ፣ ካድሬዎቹን፣የደህንነት ሃይሉን እና ሰራዊቱን በመላ ሀገሪቱ በማሰማራት፣ በየቤቱ ድንገተኛ አሰሳ እና ስለላ ለማድረግ ቆርጦ መነሳቱን ያሳያል፡፡ በመላ ሀገሪቱ አንዳች ኮሽታ ቢሰማ፣ ጸጥታ ሃይሎችየሚወስደው የጭፍለቃ ርምጃ ለዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብ ሳይደርስ አፍኖ ለማስቀረት ወስኗል፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና በአፈጻጸም መመሪያው ዘጠና ሚሊዮን የሚሆነውን የሀገሪቱንህዝብ ቀጥቅጦ ለመግዛት ሁኔታዎችን አመቻችቶ ጨርሷል፡፡ ለመጭዎቹ በርካታ ወራት የሀገሪቱ ዜጎች በሙሉ ክፉኛ ተሸማቀው፣ ርስበርስ እየተጠራጠሩ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ እንዲኖሩተፈርዶባቸዋል፡፡ አዋጁ የታሰበለትን ዓላማ መምታት አለመምታቱ ግን ወደፊት የሚታይ ነው፡፡