ዋዜማ ራዲዮ- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተባባሰው ዘውግን ያማከለ ግጭት ሀገሪቷን ወደማትወጣው ቀውስ ከመክተት ባሻገር ከጎረቤት ሀገሮች ጋር ሊያናቁረን የሚችል አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ለዚህም አንዳንድ ምልክቶች አሉ። የኢትዮዽያን ቀውስ ጎረቤት ሀገሮች በአንክሮ እየተከታተሉት ነው። ሀገሪቱ ከአስታራቂነትና ከሰላም አስከባሪነት ወደ ክፍለ አህጉራዊ የደህንነት ስጋት ከተሸጋገረች የአፍሪቃ ቀንድ ቀጠና ሊወጣው ወደማይችል አዲስ ትርምስ ይገባል። ኤርትራ ይህን ስጋቷን ከሰሞኑ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ በውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ በኩል ገልፃለች። ችግሩ ምን ያህል ቅርብ ነው? በጉዳቱ ላይ የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅተናል። አድምጡት

https://youtu.be/_ZvydtxfmjM