Bereket Simon  head EPRDF policy research center
Bereket Simon head EPRDF policy research center

በተለምዶ “ቲንክ-ታንክ” ተብለው የሚታወቁትትን የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከላት በሀገራችን መስርቶ በመምራት የህወሃቱ ሰው አቶንዋይ ገብረአብ ቀዳሚ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ-ጥር የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከላት ባይኖሯትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከፖለቲካው መድረክ የተገለሉ አንጋፋ የገዥው ድርጅት አመራሮች  ትኩረታቸውን ወደነዚህ የፖሊሲ ማእከላት ማድረግ ጀምረዋል፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ፣ በረከት ስምዖን፣ ስዩም መስፍንና ቴወድሮስ ሃጎስ በአብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ባሁኑ ጊዜ መድረኩንየተቆጣጠሩት በመንግስት አነሳሽነት የተቋቋሙት ማዕከሎች በመሆናቸው ገለልተኝነት የላቸውም፡፡ ገለልተኛ የሚባሉቱም ፈተና የበዛባቸው ናቸው።

ቻላቸው ታደሰ በነዚህ ተቋማት ዙሪያ ያሰናዳውን ዘገባ እዚህ ያድምጡት አልያም ንባብዎን ይቀጥሉ

በዓለም ላይ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከላት በመባል የሚታወቁት ተቋማት በዓለም ዓቀፍና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የፖሊሲ ምርምርበማድረግ፣ የፖሊሲ ግብዓትና ምክር በማቅረብ በፖሊሲ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ  ድርጅቶች ናቸው፡፡ ባወቃቀራቸው ከመንግስታዊመዋቅር ጋር የተሳሰሩ፣ ከፊል ነፃ፣ ገለልተኛ ወይም ለትርፍ የተቋቋሙ ኮርፖሬት ማዕከላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአፈጣጠራቸው መንግስታዊያልሆኑ ድርጅቶች ቢሆኑም ከመንግስት ወይም ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር የተለየ አጋርነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ዋነኛ ተልዕኳቸውምበመንግስትና ሲቪል ማህበረሰብ ወይም በአካዳሚክና ፖሊሲ አውጭ አካላት መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡

በሀገራችን ያሉት የፖሊሲና የምርምር ማዕከላት  ግን በጥራትም ሆነ በብዛት እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ባሁኑ ጊዜ መድረኩንየተቆጣጠሩት በመንግስት አነሳሽነት የተቋቋሙት ማዕከሎች በመሆናቸው ገለልተኝነት የላቸውም፡፡ ከግሎባል ቲንክ-ታንክ የተገኘውመረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በኢትዮጵያ ሃያ አምስት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከላት ነበሩ፡፡

ከብዛት አንፃር ሲታይ ከኢትዮጵያ በብዛት የሚልቁ ማዕከላት ያሏቸው አፍሪካ ሀገሮች አምስት ብቻ ናቸው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ደረጃ በዓለምም ሆነአህጉራዊ ደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻሉት ግን በንዋይ ገብረዓብ የሚመራው የኢትዮጵያ ልማት ጥናትና ምርምር ተቋም(Ethiopian Development Research Institute) ፣ Organization for Social Science Research in Eastern and Southern Africa ተብሎየሚታወቀው የምስራቅና ደበቡባዊ አፍሪካ የማህበራዊ ሳይንስ ምርምር ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክባለሙያዎች ማህበር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ሰላምና ደህንነት ጥናት ኢንስትቲዩት ብቻ ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ በ1999 የተቋቋመው አንጋፋው የንዋይ ገብረአብ ማዕከል ከዓለም ምርጥ 175 የፖሊሲ ምርምር ማዕከላት መካከል 172ኛ ደረጃንአግኝቷል፡፡ ተቋሙ እኤአ በ2013ም ከሃምሳ ምርጥ አፍሪካዊያን ተቋሞች መካከል አስራ ስድስተኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል፡፡ ኢንስቲትዩቱበልማት፣ ድህነት፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ተፈጥሮ ሃብትና ግብርና ላይ ምርምር በማድረግና ፖሊሲዎችን በመተንተን ለመንግስት የፖሊሲ ግብዓትያቀርባል፡፡ በከፊልም ከግብር ከፋዩ ገንዘብ በጀት ሲመደብለት የኖረ ሲሆን ላለፉት ሃያ ዓመታት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ከፍተኛሚና በመጫወት ብቸኛው ነው፡፡

መንግስታዊ ካልሆኑት ማዕከላት በደረጃ ሰንጠረዦች መግባት የቻለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር ብቻ መሆኑ ሀገሪቱእዚህ ግቡ የሚባሉ ገለልተኛ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከላት እንደሌሏት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ከአፍሪካ በየዓመቱ ቀዳሚነቱንየሚይዙት የኬንያ፣ የሴኔጋል፣ የኡጋንዳ፣ የግብፅ፣ የደቡብ አፍሪካና የጋየና ማዕከላት  ናቸው፡፡

 የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ በጅኦፖለቲካዊ አቀማመጧ ሳቢያ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምንና ባህር በር ማጣትንጨምሮ ብዙ አሳሳቢ የብሄራዊ ደህንነት አደጋዎች አሉባት፡፡ ሆኖም በወታደራዊ፣ ብሄራዊ ደህንነት፣ ውጭ ጉዳይና ወሳኝ ዓለም ዓቀፋዊጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ስመ-ጥር ማዕከላት የሏትም፡፡

በዚህ ዘርፍ በአፍሪካ ተጠቃሾቹ የደቡብ አፍሪካ፣  ግብፅና ኬንያ ማዕከላት ብቻ ናቸው፡፡ በቅርቡ ግን መንግስት በውጭ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር በቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ስዩም መስፍንየሚመራ Centre for Research, Dialogue and Cooperation የተሰኘ ማዕከል አቋቁሟል፡፡ ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ዘግይቶም ቢሆንበውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲዎች ከአህጉራዊና ክፍለ-አህጉራዊ ሁኔታዎችአንፃር ለመተንተን መዘጋጀቱን ጠቋሚ ነው፡፡

ከዚህ ዘርፍ ጋር ተዛማጅነት ያለው ሌላኛው ማዕከል በአንጋፋው የህወሃት ሰው አቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የኢትዮጵያ ውጭ ግንኙነትናስትራቴጂክ ጥናት ኢንስትቲዩት (Ethiopian Foreign Relation Strategic Studies Institute) የተሰኘው ተቋም ነው፡፡ ተጠሪነቱ ለውጭጉዳይ ሚንስቴር የሆነው ይኸው ከፊል-መንግስታዊ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም ቀደም ሲል የኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ቀንደኛደጋፊ  በነበሩት በሟቹ ፕሮፌሰር ክንፈ አብርሃ ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ዓለም ኣቀፍ ሰላምና ልማት ኢንስትቲዩት ይባል የነበረውነው፡፡

ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት ልማት ድርጅት ድጋፍ በዲፕሎማሲና ውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ትንተና፣  በአህጉራዊና ዓለምዓቀፋዊ ፀጥታ-ነክ ጉዳዮች፣ ሰላም፣ ሰላም ግንባታና ልማት ዙሪያ ጥናትና ምርምር ያደርግ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ከተመሰረተ ረጅም ጊዜቢሆነዉም ተቋሙ እምብዛም የፖሊሲ ፋይዳ ያለው ስራ ሲሰራ አይታይም፡፡  በፕሮፌሰር ክንፈ አመራር ወቅት ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴርዲፕሎማቶች በመንግስት ፖሊሲዎችና ዲፕሎማሲ ክህሎቶች ዙሪያ ስልጠና መስጠት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ብዙም ሳይገፋበት እርግፍ አድርጎ ትቶታል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፊል አስተዳደራዊ ነፃነት ያለው የሰላምና ደህንነት ጥናት ኢንስትቲዩት  ሌላኛው የጥናትና ምርምር ማዕከልነው፡፡ ተቋሙ የተቋቋመው ያኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት በነበሩት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ጠንሳሽነት ሲሆን የህወሃትአንጋፋ አመራር አባል የነበረው ሙሉጌታ ገብረሂወት (በቅፅል ስሙ) ሙሉጌታ ጫልቱ) እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ መርቶታል፡፡ ከተለያዩ ዓለም ኣቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብ ዕርዳታ የሚያገኘው ማዕከሉ በሰላምና ደህንነት መስኮች በሁለተኛና በዶክትሬት  ደረጃ ተማሪዎችንተቀብሎ በማስተማር፣ አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ምርምር በማድረግና የተለያዩ  ሪፖርቶችን በማውጣት ተሰማርቷል፡፡ ላለፉትጥቂት ኣመታትም የመከላከያ ከፍተኛ ሃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ሲያሰለጥን ኖሯል፡፡ ስራ ላይበሚያውለው የሰልጣኞች ቅበላ መስፈርቱ ተደጋጋሚ ወቀሳ የሚነሳበትም ለዚሁ ነው፡፡

ተቋሙ በዋናነት በመደበኛ ትምህርት ላይ ያተኮረ አካዳሚክ ተቋም ቢሆንም ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ፕሮግራም የተሰኘ ፕሮግራም ቀርፆ በሰላምና ደህንነት ዙሪያ አህጉር ዓቀፍ ምርምሮችን በማድረግለህብረቱ የፖሊሲ ግብዓት በማቅረቡና ስልጠናዎችንም መስጠት በመጀመሩ እንደ ጥናትና ምርምር ማዕከል እንዲታይ አስችሎታል፡፡ለህብረቱና ክፍለ አሁጉራዊ ድርጅቶችም አጫጭር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታትም በኢትዮጵያናደቡብ ሱዳን የግጭት ካርታና ግጭት ትንተና ጥናቶችን አካሂዶ የፖሊሲ ግብዓት አቅርቧል፡፡በሱማሊያም የፖሊሲ ምርምሮች ያካሂዳል፤ባለሙያዎቹም መንግስትን ያማክራሉ፡፡ የአቶ መለስ ጥንስስ የሆነውን “ጣና ፎረም” የተሰኘውን ዓመታዊ ኢመደበኛ የአፍሪካ ቀንድመሪዎች ስብሰባ የሚያስተባብረውም ይኸው ተቋም ነው፡፡

ከአቶ መለስ ህልፈት ማግስት ደሞ አንጋፋዎቹ የገዥው ድርጅት ቁንጮዎች በአቶ በረከት ስምዖንና አባይ ፀሃዬ የሚመራ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የተሰኘ አዲስ ተቋም ተቋቁሟል፡፡ ሁለቱ ጎምቱዎች ከየድርጅቶቻቸውና ኢፊሴላዊ መንግስታዊ ስልጣናቸው በጡረታየተገለሉ ቢሆኑም በማዕከሉ በኩል ለገዥው ድርጅት ርዕዮተ-ዓለምና ፖሊሲ ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆነው መጥተዋል፡፡

ይህም ገዥውድርጅት ምን ያህል ከነባር አመራሮቹ አስተሳሰብ መላቀቅ እንዳልፈለገ አስረጂ ነው ይላሉ ታዛቢዎች፡፡ ተቋሙ እጁን ያሟሸው በያዝነውዓመት መባቻ ላይ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ናሙና ጥናት በማካሄድ ሲሆን በጥናቱ ላይ ከፍተኛ ባለስልጣናት ያደረጉትውይይትም በቀጥታ በቴሌቪዥን መተላለፉ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፡፡

የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽንም የህወሃት/ኢህአዴግ ሌላኛው የጥናትና ምርምር ማዕከል እየሆነ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንጋፋውየህወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ቴወድሮስ ሃጎስ ከፓርቲ ኃላፊነታቸው ለቀው ፋውንዴሽኑን እንዲመሩ መመደባቸው በነባሮቹፖለቲከኞች አማካኝነት መንግስታዊ ፖሊሲን በእጅ አዙር ለመቆጣጠርና ሃብትን ለመቀራመት የሚደረገው ሽኩቻ አካል ተደርጎ ሊወሰድይችላል፡፡

ኢህአዴግ-መራሹ መንግስትም ራሱ ከሚያቋቁማቸው ማእከላት ጋር እንጂ ከገለልተኛ ፖሊሲ ማዕከላት  እንዲፋፉ የሚፈልግአይመስልም፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ካሉ ማዕከላት ጋር ያለው የስራ ግንኙነቱም በጣም ልል ነው፡፡ ከኢኮኖሚባለሙያዎች ማህበር ሌላ እዚህ ግባ የሚባል ለትርፍ የተቋቋመ የፖሊሲ ጥናትና ማዕከል የለም፡፡ በመሆኑም ፖሊሲ በማመንጨትም ሆነበፖሊሲ ሃሳቦች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ውስጥ ከመንግስት ባለስልጣናት ውጭ ገለልተኛ ማዕከላት ተሳትፎ ማየት የማይታሰብ ሆኗል፡፡

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥመ ሆነ ከሀገር ውጭ በርካታ ወታደራዊ ጠበብቶች፣ ምሁራንና ስመ-ጥር አንጋፋዲፕሎማቶችን አፍርታለች፡፡ ምንም እንኳ ፖሊሲው አመቺ ቢመስልም ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ግን የሀገሪቱን የሰው ኃይል ሃብትብሄራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል፡፡ የኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ፖሊሲ አወጣጥ አሁንም በፖሊሲ ጥናትናምርምር ማዕከላት ሽፋን በገዥው ፓርቲ ጥቂት ቁንጮዎች በእጅ አዙር ተይዟል፡፡ በመሆኑም በሁሉም ዘርፎች የሚመነጩ የፖሊሲሃሳቦችም ሆኑ በፖሊሲ ላይ የሚደረጉ ምርምሮችና ውይይቶች ከመንግስትና ፓርቲ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ሊወጡ አልቻሉም፡፡

መንግስት ማዕከላቱን የፖሊሲውን ትከከለኛነት ለዓለም ኣቀፍ ድርጅቶችና ምዕራባዊያን ዕርዳታ ለጋሽ ሀገሮች ለማረጋገጥ እንደ መሳሪያእየተጠቀመባቸው እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ በሌላ በኩል ከፓርቲውና መንግስት ስልጣን ጡረታ የሚወጡ የድርጅቱ አንጋፋ ሰዎችበእጅ አዙር በመንግስት ፖሊሲ ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚያስችላቸውን መድረኮች ማመቻቸታቸውን ያሳያል፡፡ አካሄዱ የጡረታ መውጫናኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ማካበቻ አዲስ ስልት እንደሆነም ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ማዕከላት ለሚያደርጉት ጥናትና ምርምርከውጭ ምንጮች የገንዘብ ዕርዳታ እንዲያገኙ ህጉ ይፈቅድላቸዋልና፡፡

አሁንም በፖሊሲ ጥናትና ርምር ማዕከላት እየተሰባሰቡ ያሉት በብቃታቸው የተመሰከረላቸው አንጋፋ ምሁራን፣ ባለሙያዎችናዲፕሎማቶች ሳይሆኑ የገዥው ድርጅት የቀድሞ አመራሮች መሆናቸው ኢህአዴግ የፖሊሲ ሃሳቦችን በማመንጨትና በፖሊሲ ላይ ውይይትማድረግ ከእጁ ሳይወጣ ተቆጣጥሮ ለመቀጠል ያለውን ፅኑ ፍላጎት ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡