Molla Asgedom
Molla Asgedom

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀምንበር ሞላ አስገዶም ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ግንኙነት እንደነበረው ተናግሯል፣ በተግባርም አረጋግጧል።

ግንኙነቱ አንድ አመት ይሁን ሰሞነኛ የተምታቱ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ሞላ አስገዶም በኤርትራ ያሉ ተቃዋሚዎችን “እንዳያገግሙ አድርጎ” የማምከን ተልዕኮ ቢሰጠውም ተልዕኮውን ሳይፈፅም ለመሸሽ ተገዷል። ቁጥራቸው ከገለልተኛ ወገን ያልተረጋገጠ እስከ ስድስት መቶ ወታደሮች አብረው ኮብለለዋል።

ትህዴን ግን ኮብላዮቹ ከሀምሳ አይበልጡም ብሏል። ሞላ የኢትዮዽያ መንግስት ትክል ከነበረ አሁን ለመሸሽ ለምን መረጠ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ይፈልጋሉ። ዋዜማ ሬዲዮ ከተለያዩ ምንጮች የተለያዩና የተቃረኑ እንዲሁም በፖለቲካዊ ፍላጎት የታጀቡ ምለሾችን አግኝታለች። ማጣራት የሚፈልገውን ትተን ከሁለትና ከዚያ በላይ ምንጮች የነገሩንንና አቅም በፈቀደ የመረመርነውን መረጃ ብቻ መነሻ አድርገን ተከታዩን ዘገባ አሰናድተናል።