clapham-the-horn-of-africa-rgb-webዋዜማ ራዲዮ- እውቁ የፖለቲካ ተንታኝና ምሁር ክርስቶፈር ክላሀም በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪቃ ጉዳይ ላይ ያተኮረ አዲስ መፅሀፍ ፃፉ።
የአፍሪቃ ቀንድ፤ ሀገር ግንባታና ውድቀት The Horn of Africa: State Formation and Decay የሚል ርዕስ የተሰጠው መፅሀፍ ሰፊውን ሽፋን ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ የሰጠ ሲሆን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ አመስራረትና ገናናነትን በኋላም ሀገሪቱ የገጠማትን የሀገር ግንባታ ፈተና ይዳስሳል። መፅሀፉ በአብይ ትኩረቱ የአፍሪቃ ቀንድ ከሌላው አካባቢ ሁሉ በተለየ ለምን የፖለቲካ ቀውስ ማዕከል እንደሆነ የሚተነትን ነው።
የቀዝቀዛው የአለም ጦርነት ያበቃበትን ጊዜ እንደ ማጣቀሻ በመውሰድ ከደርግ ውድቀት በኋላ የተሰራችው ኢትዮጵያ የገጠማትን ድርብርብ ፈተና ይዳስሳል።
ሶማሊያ ከቀዝቃዛው ጦርነት ተከትሎ የገጠማት መፈራረስና እስከዛሬም ልትወጣው ያልቻላቸውን የፖለቲካ ቀውስ እንዲሁም የኤርትራን መወለድ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ጋር የነበራቸውን ተቃርኖ ይተነትናል።
ክርስቶፈር ክላሀም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ላይ የተኮሩ Transformation and Continuity in Revolutionary Ethiopia(1988), Africa and the International System (1996), and African Guerrillas (1998) የተሰኙ ሁነኛ መፅሀፍትን አበርክተዋል፣ በርካታ የጥናት ፅሁፎችንም ፅፈዋል። በተለይ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለውን ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግን በተመለከተ ከብዙዎቹ የውጪ ሀገር ተንታኞች የተለየና የጠለቀ አስተያየት አላቸው። ስድስት ምዕራፍ ያለው ይህ መፅሀፍ ከየካቲት ወር ጀምሮ በገበያ ላይ ይውላል። ምሁሩ በርካታ የአፍሪቃ ፖለቲካን የተመለከቱ መፅሀፍትና ጥናቶችን አበርክተዋል።