FILE- UAE Navy
FILE- UAE Navy

ኤርትራ በየመን ቀውስ ዙሪያ ከሳዑዲና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጎን መሰለፏን የሚያረጋግጡ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሶስት የጦር መርከቦች አሰብ ወደብ የደረሱ መሆኑን ዋዜማ ያገኘችው የሳተላይት መረጃ ያመለክታል። የመንግስታቱ ድርጅት በበኩሉ አራት መቶ የኤርትራ ወታደሮች በየመን በውጊያ እያተካፈሉ ነው ብሏል። ኤርትራ መረጃውን በይፋ አላስተባበለችም። የኤርትራ ወደ የመን ቀውስ መግባት ከምዕራቡ አለም ጋር ለመቀራረብ በር ሊከፍትላት ይችላል የሚል ግምት አለ። ለኢትዮዽያ ይህ መልካም ዜና አይደለም። አርጋው አሽኔ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል፣ አድምጡት