President-Isaias-in-New-York-Cityከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማግስት ሆድና ጀርባ የሆኑት አሜሪካና ኤርትራ በተለያየ መንገድ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጮች መታየት ጀምረዋል። ኤርትራ በሶስተኛ ወገን በኩል ፍለጎቷን ብትገልፅም አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት አቋም እያንፀባረቀች ነው። አሜሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሸሪኮቿ በየመን የተከሰተወን ቀውስ በጦርነት መፍታት ባለመቻላቸው ኤርትራን ጨምሮ ከአካባቢው ሀገራት ጋር ለመተባበር እየተዘጋጁ ነው። በቅርቡ ከሱዳን ጋር ግንኙነቷን በማሻሻል የልዑካን ቡድን ወደ ካርቱም የላከችው ዋሽንግተን ወደ አስመራ መዝለቁ ቀላል ውሳኔ አይሆንላትም የሚሉ አሉ። ከኢራንና ኪዩባ ጋር አዲስ ምዕራፍ የከፈተችው አሜሪካ ወዳጇን ኢትዮዽያን ሳታስቀይም አስመራ ትዘልቅ ይሆን? አርጋው አሽኔ ያዘጋጀውን አድምጡ