UN-Human-Rights-Council
UN-Human-Rights-Council

በአፋኝነቱና በከፋ የሰብዓዊ መብት ረገጣ የሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጧል ከሰሞኑ። ሁኔታው አስገራሚም አሳዛኝም ገፅታ አለው። ለመሆኑ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት እንዴት ያለ ነው?

ዳንኤል ድርሻ ያዘጋጀውን መዝገቡ ሀይሉ ያቀርበዋል-አድምጡት

በየጊዜው በምዕራባውያን መንግስታት እና ለዲሞክራሲ መስፈን ዘብ በቆሙ የመብት ተሟጋች ተቋማት በጨቋኝነትና አፋኝነ እና በአብይ ሰብዓዊ መብት ረገጣ የሚወገዘው የኢትዮጵያመንግስት የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት 2ዐ16 ምክትል ሊቀ መንበር ሆና መመረጥ  እያነጋገረ ነው ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት  የቀድሞውን የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተክቶ ሥራ የጀመረው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጠር በ2006 ዓ.ም ነበር፡፡በበርካታ ቅሌቶች ተዘፍቆ የኖረው  የመንግሥታትን መብት ጥሰት ከማጋለጥ ይልቅ በመሸፋፈፈንና ማለባበስ ታሪኩ የሚታወቀው ኮሚሽን  ፣ ለበርካታ ዓመታት የተጓዘው የጉልበተኞችመሳሪያ ሆኖ ነበር ፡፡ ኮሚሽኑን የተካው ምክር ቤ የተመድ ጠቅላላ ሸንጎ በ1948 ዓ ም ያጸደቀውን መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ለማስፈጸም እተጋለሁ ብሎ ሲነሳ ከፊተኛው አሰራርበተለየ ሁኔታ ለመብት መከበር  የሚያስተባብር መሪ ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበትም ነበር፡፡

ገና ከጅምሩ የአባል ሃገራትን ምልመላ በተመለከተ የያዘው አቋም ግን የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አመኔታ ጥያቄ ላይ የጣለ ነበር፡፡ የተሻለ አና የጠነከረ መተዳደሪያ ይዞ ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ መጠነኛ ጥገናዊ ለውጥ በማከል ሥራውን መቀጠሉም ተጨማሪ ችግር ነበር፡፡ ለአዲሱ ምክር ቤት አባልነት በዕጩነት የሚቀርቡ ሃገራት በከፋ የሰብዓዊ መብት ረገጣአለመሳተፋቸው ሊጣራ ይገባል የሚለው ሃሳብ በአሜሪካ ቀርቦ የነበረው ረቂቅ ያኔውኑ ውድቅ መደረጉም ምክር ቤቱ የት ድረስ መሄድ እንደሚችል ጠቋሚ ሆነ፡፡

ለአባልነት የቀረበው መስፈርትም ለጉልበተኛ መንግሥታት የተመቻቸ ሆነ፡፡ አርባ ሠባቱ የምክር ቤቱ አባል ሃገራት በ”ፍትሐዊ” ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ላይ ተመርኩዞ እንዲመረጡመደረጉ ፈተናውን አከበደው፡፡ ሃያ ስድስቱን ወንበር ኤዥያና አፍሪካ ከተቀራመቱት ከምክር ቤቱ አጠቃላይ አርባ ሰባት ወንበር ውስጥ ስምንቱ ለላቲን አሜሪካ፣ ሠባቱ ለምዕራባውያን፣ስድስቱ ደግሞ ለምስራቅ አውሮፓ እንዲከፋፈል መደረጉም የፈጠጠውን ሃቅ አሳየ፡፡ የአምባገነኖች መናኸሪያ የሆኑት አፍሪካና ኤዥያ ብቻቸውን ሃያ ስድስት ወንበር መያዛቸው የሰብዓዊመብቶች ምክር ቤቱ በሰብዓዊ መብት ረጋጮች ቁጥጥር ሥር የመውደቁ ትልቅ ማሳያ ነበር፡፡

ያኔውኑ የምክር ቤቱ አባልነት ዕድልን ካገኙት መሐል ቻይና፣ ሳዑዲ አረቢያና ኩባን የመሳሰሉ አምባገነኖች የገቡት ቃል ኪዳን  ዛሬም ድረስ አለመከበሩ በራሱ የምክር ቤቱ አቅምና ክብደትማረጋገጫ ሆኖ  ይወሰዳል፡፡ ለአብነትም በዚያ ወቅት ምርጫ ከመካሄድ አስቀድሞ የቻይና መንግስት በገባው ቃል ኪዳን የቻይናን ሕዝብ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ለማስከበር ያለውንቁርጠኝነት በአደባባይ የገለጸ ሲሆን፣ ኩባ በበኩሏ ለሕዝቧ ሲቪልና ፖለቲካ ነጻነት መረጋገጥ ቃል ገብታለች፡፡ ይሕ ቃል ከተገባ ከአሰርት ዓመታት በኋላ የቻይና እና የኩባ ሕዝብ ያሉበትንነባራዊ ሁኔታ መከታተልና ባለፉት ዓመታት እንደተጠቀሱት ባሉ ሃገራት ሲፈጸሙ የነበሩትን የመብት ጥሰቶች መቃኘት በኮሚሽኑ ምትክ የተመሰረተው ምክር ቤት የረባ ሚና ከመጫወትውጪ መሆኑን ያጋልጣል፡፡

በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ በርካታ መጽሐፍትን ለንባብ ያበቁት የላቲን አሜሪካው ቴድ ፒኮ አሰራሩን ከፈተሹ በኋላ “የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በጄኔቫ ከተማ ከመሰብሰብ ያለፈ አቅምየሌለው፣ ከታላላቅ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይልቅ ለስላሳ ጉዳዮችን የሚነቅስ፣ ከግድያና ፍጅት ይልቅ የሕጻናት መብቶች ጉዳይ ያስጨነቀው ለመምሰል የሚጥር፣ በእንጭፍጫፊ ጉዳዮችላይ ተከራክሮ ከመበተን ያለፈ ተጽዕኖ ማሳረፍ የማይችል” በማለት ይገልጹታል፡፡

በሎከርቢው አውሮፕላን ፍንዳታ ዋና ተጠያቂ የነበረችው ሊቢያ በ2003 የፈረሰው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን በሊቀ መንበርነት መምራቷን በማውሳት ኃያላኑ ጭምር በሰብዓዊ መብትላይ ምንኛ እንደዘበቱ ማስታወስ አይገድም፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ  በዳርፉር ሰብዓዊ መብት ጥሰት ዋና ክስ የቀረበባት ሱዳን የዚህ ምክር ቤት አባል ለመሆን አቅርባው የነበረው ጥያቄያበሳጫቸው የአሜሪካው አምባሳደር ስብሰባ ረግጠው ለመውጣት የገፋቸውን ብስጭት መዘከርም አይገድም፡፡

በሥራ ላይ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን ስናይ ደግሞ በሽር አል አሳድ ሶሪያን የምክር ቤቱ አባል አድርጎ ለማስመረጥ ያደረጉት እንቅስቃሴን በመግለጽ የቀድሞው ኮሚሽን ከአሁኑምክር ቤት ያለውን ልዩነት ፈልጎ ለማውጣት ያዳግታል፡፡አምባገነን መንግሥታት ምክር ቤቱን ለከለላ መጠቀሚያነት ምን ያሕል እንደሚጓዙም ማሳያ ይሆናል፡፡ አሁን በቅርቡ  በመስከረም ወር ሳዑዲ አረቢያ የምክር ቤቱ የኤክስፐርቶች ቡድን ሊቀ መንበር ሆና በተመረጠችበት ወቅት የተነሳውን አቧራም መጥቀስ አያስቸግርም፡፡

በጄኔቫ የሳዑዲ አምባሳደር ፋይዘል ቢን ሃሰን ገለልተኛ የተባሉ ኤክስፐርቶችን የሚመራው መድረክ ሊቀ መንበር ሆነው መመረጣቸውን የተቃወሙት ዩኤን ዎች የተባለው ተቋም ዳይሬክተር “በዚህ ዓመት ከ ISIS በላይ የበርካታ ሰዎችንሕይወት በሰይፍ የነጠቀ ሃገርን ለቁልፍ ሰብዓዊ መብት መሪነት ተመድ መምረጡ ታላቅ ቅሌት ነው፤” ሲሉ ነቅፈው  ከነዳጅ ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ( ፔትሮ ዶላር)  እና ፖለቲካው ሰብዓዊመብትን እንደደፈጠጡ አስረድተዋል፡፡

የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ለ2ዐ16 የምክር ቤቱ አባልነት ዕጩዎችን ባቀረበበት ወቅ ሃያ አንዱንም ዕጩዎች የገመገሙት ሶስት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ማለትም ዩኤን ዎች፣ሂዩማን ራይትስ ፋውንዴሽን እና ላንቶስ ፋውንዴሽን ባወጡት ቅድመ መግለጫ ለውድድር ከቀረቡት ውስጥ ዘጠኙ ሃገራት ፈጽሞ ለዚህ ወንበር የሚመጥኑ አይደሉም ብለው ነበር፡፡ከዘጠኙ ውስጥ ሰባቱ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ፣ ቬኑዙዌላ፡ ኢኳዶር፣ ቡሩንዲ፣ ቶጎ እና ኪርጊዚስታን የቀረበበቸው አስከፊ የመብት ጥሰት ሪከርዳቸው ከመመረጥአላገዳቸውም፡፡ አስገራሚው ጉዳይ ሶስቱ ተቋማት የሃሃገራቱን የመብት ጥሰት ዶሴ የወሰዱት ከራሱ ከተመድ መሆኑ ነው፡፡

ላለፉት አርባ ዓመታት መቀመጫውን ዋሽንግተን ከተማ አድርጎ የሃገራትን የፖለቲካ መብትና ሲቪል ነጻነት ሲገመግም የቆየው ፍሪደም ሃውስ እንደየ መንግሥታቱ ሰብዓዊ መብት አያያዝ”ነጻ”፣ “ከፊል ነጻ” እና “ነጻ ያልሆኑ” በማለት ደረጃቸውን ያሳውቃል፡፡ በፍሪደም ሃውስ ወቅታዊ መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በምክትል ሊቀ መንበርነት በተመረጠችበት አዲሱ ምክር ቤት ውስጥየሰው ልጆችን መብት አክብረው ያስከብራሉ በሚል “ነጻ” የተሰኘ ደረጃ የተሰጣቸው አስራ ስምንቱ ብቻ ናቸው፡፡ የተቀሩት ሃያ ሰባት ሃገራት “ነጻ ያልሆኑ” ወይም “ከፊል ነጻ” በተሰኘ ማዕረግየሰብዓዊ መብት ረጋጭና ጣሺነታቸው የተመደቡ ናቸው፡፡

በፍሪደም ሃውስ መመዘኛ በአዲሱ ምርጫ ከአስራ ሶስት ወንበሮቿ አምስት ቦታዎችን ለመተካት አምስት ዕጩዎችን ካቀረበችው አፍሪካ ሁለቱ ማለትም ኢትዮጵያና ቡሩንዲ “ነጻ ያልሆኑ”ተብለው ሰብዓዊ መብትን በመርገጥ በቀዳሚ ደረጃ የተቀመጡ ናቸው፡፡ ዩ.ኤን ዎች የተሰኘው የመብት ተሟጋች ዓለም አቀፍ ቡድን ተቀዳሚ ዳይሬክተር ሂለር ኑዌር ይሕን የምርጫ ዕለት”የሰብዓዊ መብት ጨለማው ቀን” ሲሉት፣ አጠቃላይ ሂደቱን ደግሞ ቧልት ብለውታል፡፡

በማለት የ2015 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታን የዳሰሰው ሂዩማን ራይትስ ዎች “ለጋሾች የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ድምጽ አያሰሙም፤ ተፈጽመዋል የተባሉበደሎችን በተመለከተ ለማጣራት ብዙም ትርጉም ያለው እርምጃ አልወሰዱም። ፡፡ “ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ዩኒቨርሳል ፔሬዲክ ሪቪው(Universal Periodic Review) ግምገማ በግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. ቀርባ እንደነበር ያስታወሰው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም… “በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ውግዘት እየቀረባበቸውየሚገኙ አፋኝ ሕጎችን ለማሻሻል የኢትዮጵያ መንግስት ምንም የፈቃደኝነት ምልክት አላሳየም።” ሲል መንግሥት ሰብዓዊ መብትን ሕግጋትን በመከለስ ረገድ ያለውን ደንታ ቢስነትአጋልጧል፡፡