ዋዜማ ራዲዮ- ገዥው ፓርቲ ለዓመታት ሲወገዝበት የነበረውን ተቀናቃኞቹንና ትችት የሰነዘሩበትን ለማሰቃየት የሚጠቀምበትን የማዕከላዊ እስር ቤት ዝግቶ ወደ ሙዚየምነት ለመለወጥ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

የፖለቲካ እስረኞችንም እፈታለሁ ሲል ቃል ገብቷል። በርካቶች የድርጅቱን እርምጃ በበጎ ቢመለከቱትም ተግባራዊነቱ ላይ ጥርጣሬ አላቸው። የሚፈቱት እስረኞች እነማን ናቸው? መልስ የሚፈልግ ጥያቄ ነው። ይህ እርምጃ አዲስ የፖለቲካ ሽግ ግር ጅማሮ ነውን ወይስ ገዥው ፓርቲ ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት የዘየደው መላ? ይህንንና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተን በዚህ የዋዜማ ራዲዮ “በነገራችን ላይ”  መሰናዶ እንወያያለን። አድምጡት