Young Oromo Protestors SM
Young Oromo Protestors SM

(ዋዜማ ራዲዮ) በሀገሪቱ ያለው ጭቆና ገፈት ቀማሽ የሆነው ሁሉም ኢትዮዽያዊ ሆኖ ሳለ ስለምን ሁሉም በጋራ ተቃውሞውን ማሰማት ተሳነው? የሚለው ጥያቄ የሚያናድድም የሚያስፈራም ድባብ አለው። በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ደም እየከፈለ ባለበት በዚህ ጊዜ አብሮ ለመቆም የሚሞክር የሌላ አካባቢ እንቅስቃሴ አለማየት ጉዳዩን በአፅንኦት እንድንመለከተው ግድ ይለናል። ዋዜማ ስለምን ሌላው ህዝብ ከኦሮሞ ወገኑ ጎን ለመቆም ተሳነው? ለሚለው ምላሽ ሊሆኑ የሚችሉ የመነሻ ሀሳቦችን ታነሳለች። ፕሮግራሙን አድምጣችሁ የናንተን ሀሳብ ደግሞ አጋሩን።