Khartoum
Khartoum

ዋዜማ ራዲዮ- የሱዳን መንግስት በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ስልፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን በእስራት በጅራፍና በገንዘብ ቀጣች።
የሱዳን መንግስት በቅርቡ ያደረገውን የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በመቃወም መንግስታቸው ጣልቃ እንዲገባ ለመጠየቅ የካቲት ቀን በኢምባሲው ዳጃፍ ከተሰለፉ አንድ ሺህ ያህል ስዎች መካከል አምስት መቶ ያህሉ በሱዳን የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ውለው አርባ የጅራፍ ግርፋትና አስራ አምስት ሺህ ብር ቅጣት አልያም የሁለት ወር እስራት ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
በሱዳን የመኖሪያ ፈቃድ ዋጋ 46 ዶላር የነበረ ሲሆን በቅርቡ 308 ዶላር እንዲሆን መደረጉን ራዲዮ ዳባንጋ ዘግቧል።
ኢትዮጵያውያኑ የዋጋ ጭማሪው እንዲቀነስላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ከጎናቸው እንዲቆም ለመማፀን ስልፍ እንደሚያደርጉ አስቀድመው አሳውቀው ነበር። በርካቶች ታሳሪዎች አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንዳሉ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የካርቱም ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ተናግረዋል።
በሱዳን እስር ቤቶች ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በተለያየ ክስ በወህኒ እንደሚገኙ ይታወቃል።