Cop 21ብዙ የተወራለትን የኮፐንሀገን ጉባዔ አስታወሳችሁት?… የኢትዮዽያ የልዑካን ቡድን በቤተ መንግስት አሸኛኘት ተደርጎለት ነበር ወደ ዴንማርክ መዲና ኮፐንሀገን ያቀናው። ጉባዔው በአለም የአየር ፀባይ ችግር (Climate Change) ላይ የሚነጋገር ነበር። ጉባዔው በየአመቱ የሚካሄድ ይሁን እንጂ የኮፐንሀገኑ ብዙ የተወራለትና በውዝግብ የታጀበ ነበር። የቀድሞ የኢትዮዽያው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አፍሪካ የሚገባትን ካሳ ካለገኘች ስብሰባውን ረግጠን እንወጣለን በሚል ማስፈራሪያ በመታጀብ የአፍሪካን ልዑካን መርተው ነበር። ውጤቱ ግን የተለየ ነበር። አሁን ደግሞ የፓሪሱ ጉባዔ ሊካሄድ ቀናት ቀርተውታል። በጉባዔዎቹ የመሳተፍ ዕድል ያገኘው አርጋው አሽኔ ያሰናዳውን ዘገባ እነሆ።