ዋዜማ ራዲዮ- አልጀዚራ በአዲስ አበባ ቢሮውን መክፈቱ ለአፍሪቃ ህብረት ጉዳዮች ትኩረት ለመስጠት አቅዶ ነው የሚለው መከራከሪያ ሞኛ-ሞኝነት ይመስላል። ይልቁንም የሰሞኑ የአልጀዚራ ዘገባዎችን ላየ ምስጢሩ ይገለፅለታል። ኤርትራዊው የአልጀዚራ የአዲስ አበባ ቢሮ ሃላፊም ቢሆኑ ሻዕቢያና ወያኔን ገና ጫካ ሳሉ ጀምሮ የሚያውቁና ከዐረቦቹ ጋር የሚያገናኙ ጉዳይ አስፈፃሚ ነበሩ። ኳታር በአዲስ አበባ ወደ አስመራ ስታጠቃ ንዝረቱ ሳዑዲና ዱባይ ይደርሳል በሚል ስሌት ነው። ቱርክ በሶማሊያ አዲስ ጦር ሰፈር ከፍታለች። የአፍሪቃ ቀንድ ወደ አደገኛ የጦር መንደርነት እየተቀየረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን በራሷ ውስጣዊ ጉዳይ ተተብትባ ለአካባቢያዊው ነባራዊ ሁኔታ መልስ መስጠት ተስኗት ይታያል። ይህ መሰናዶ አንዳንድ ነገሮችን ያነሳል፣ ያድምጡት።

https://youtu.be/mU8wmWsf51M