Home Talking points Benegerachin Lay-Discussion በነገራችን ላይ- ኢህአዴግና ሀያ ሚሊየኖቹ !

በነገራችን ላይ- ኢህአዴግና ሀያ ሚሊየኖቹ !

March 26, 2016 4
Share!
Photo FILE

Photo FILE

በሀገሪቱ አሁን የተከሰተው የረሀብ አደጋ በህዝብ ቁጥርና ስፋት በታሪክ ተወዳዳሪ የለውም። አሁን የተረጂዎች ቁጥር 20 ሚሊየን ደርሷል። ለመሆኑ ረሀቡን በተመለከተ የመንግስት ምላሽ፣ የለጋሾች አቋምና በአጠቃላይ ለችግሩ የተሰጠው ትኩረት አደጋውን የሚመጥን አይመስልም። በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን አሰባስበን ውይይት አድርገንባቸዋል። አድምጡት ተወያዩበት አጋሩት

 Related

4 Comments

  1. ቢንያም (The Fugitive) March 30, 2016 at 11:56 am

    በ“ድርቅ” እና በ“ረሀብ” እንዲሁም በ“ጠኔ” መካከል ሰማይ ከመሬት እንደሚርቅ ትልቅ ልዩነት አለ::በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ድርቅ ነው ካልን እንደ አለም አቀፎቹ የመገኛ ብዙሀን እና አምባገነኑ የህውሀት ስረውመንግስት የዜና ዘገባ መሰረት ድርቅ በሰሜን አሜርካ በካሊፎርንያ፣በአውስትራሊያ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ አለ በሚል ፈሊጣዊ አባባል ደጋግመው በጂኦፓለቲካዊ ጥቅም ታውረው ያደነቁሩናል::በእርግጥ እውነት ነው በእነዚህ አገሮች ማለትም በሰሜን አሜርካ በካሊፎርንያ፣በአውስትራሊያ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት በመዝናኛ ቦታቸው እየተንሸራተቱ የሚጫወቱበት ውሀዎቻቸው ደርቀዋል እንጂ በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው፣እንሰሳ እና የምግብ አለመኖር ወይንም የምግብ እጥረት በስህተት አልታየም:: ስለሆነም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው “ድርቅ” ወይንም “ረሀብ” ሳይሆን ያለው “ጠኔ” ነው::ምክንያቱም እውነተኛ ድርቅ ማለት የምግብ እጥረት ማለት እንጂ የምግብ አለመኖር ማለት አይደለም::አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁናቴ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 20 ሚሊዮን በላይ ምስኪን ወገኖቻችን ምግብ በአፋቸው ከገባ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ስላስቆጠሩ ምግብ ማለት እንኳ ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙን በቅጡ አያውቁትም አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተው ከረሀብ ወደ መጨረሻው የመብል ጣረ ሞት ወደ “ጠኔ” ከፍ ብሏል ስለሆነም በሀገራችን ከአጥንት በላይ ማሰብ የማይችሉ ውሾች የፈጠሩት ድርቅ ወይም ረሀብ ሳይሆን “ጠኔ” ነው::የረሀብ እና የጠኔ በአንድ ሀገር መኖር የጂኦፓለቲካ ጥቅሙ የጎላ ነው::ለዚህም ነው አንጋፋው ዲፕሎማትና የፓለቲካ ሳይንቲስት ሄነሪ ኪሲንጀር የረሀብን እና የጠኔን ለፓለቲካዊ ጥቅም እድሜ ማራዘሚያ አስፈላጊነት ሲመክር እንዲህ በማለት ነበር “ምግብን ከተቆጣጠርክ ህዝቡን ትገዛዋለህ!” ይህ ነው እውነታው ወገኖቼ::ሌላው መስፍኔ ከዚህ እንዲህ ብሎ በተናገረው፦ “በ50 ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የጤናው ዘርፍ በእድገትም ሆነ በጥራት አድጓል ስለሆነም በረሀብ ምክንያት የሚሞት ህዝብ የለም እንዲኖርም የምእራባውያን ሀገራት አይፈልጉም!” ቃል ላይ የራሴን አስተያየት ለመስጠትም ጭምር ነው::በአንድ ወቅት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካው መሪ ታቦ ሜባኪይ ለተባበሩት መንግስታት የህብረቱ ስብሰባ ላይ እንዲህ ብለው ተናግረው ነበር “በአፍሪካ ውስጥ ኤድስ የለም ያለው ረሀብ ነው::አንድ ሰው በቂ ምግብ ካላገኘ ጉንፋን እንኳ በእራሱ ኤድስ በሽታ ሆኖ ይገድለዋል!” ይህ የታቦ ሜባኪ አባባል በእርግጥ በምግብ ጥጋብ በሚታወቁ የበለጸጉ አገሮች ጥሩ ምስክር ነው::ምክንያቱም በበለጸጉት አገሮች በኤድስ በሽታ ምክንያት የሚሞት ሰው የለምና::ምክንያቱም ኤድስ በሽታ በበለጸጉ አገሮች ስለሌለ ሳይሆን በእነዚህ አገሮች ውስጥ የምግብ እጥረት፣ረሀብ እና ጠኔ ስለሌለ ብቻ ነው::ስለሆነም በየትኛውም በሽታ ምክንያት የሚከሰቱ የሞት አደጋዎች ዋና መነስኤያቸው የህክምና ሳይንሳዊ ግብአቶች እጥረት እና እጦት ሳይሆን ለሰውነት የሚያስፈልጉ የተመጣጠነ ምግብ አለመኖር ነው::ሌላው ሁላችንም እንደምናውቀው የአለማችን “ኢሊቶች” ዋና አለም አቀፍ አጀንዳቸው የሆነው “የአካባቢ ጥበቃ” ዋና ምክንያት እና መፍትሄ አድርገው ያቀረቡትም የአለም የስነህዝብ ቁጥር እጅግ መጨመር በተለይም የሶስተኛ አለም ደሀ አገሮችን ህዝብ በተለያዩ ሰው ሰራሽ ሳይንሳዊ እና ባውሎጂካሊ ትጥቆችን በመፍጠር ማለትም በጦርነት፣በረሀብ፣በጽንስ ማስወረድ፣በበሽታ እና ተፈጥሮን እራሷን በማዛባት የሰውን ቁጥር መቀነስ እንደሚቻል በተለያዩ መድረኮች ሲገልጹ የነበረ የክፍለ ዘመናችን ዋና አጀንዳ ሲሆን እንዲሁም ካለፉት 60 አመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሆነ የተለያዩ ሰነዶች እንዲሁም ከ“አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት” The New World Order የመንግስታቸው ማኒፌስቶ ላይ በግልጽ ጽፈውታል ይህንን እውነት ለማወቅ ስለ“አዲሱ የአለም መንግስት ስርአት” The New World Order አጀንዳ ከጎግል በመጎልጎል ብዙ መረጃ ማግኘት ይቻላል::በአለም ላይ በስነ ህዝብ ቅነሳ ፕሮግራም ግዙፍ ገንዘብ መድበው በግለሰብ ስም እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት እንደ ቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የመሳሰሉት ከወሊድ መቆጣጠሪያ ያመለጠውን ነፍስ በጽንስ ማስወረድ ከጽንስ ማስወረድ ያመለጠውን የህጻን ነብስ በድርቅ፣በረሀብ እና በጠኔ ማስወገድ አሊያም በጸረ ክትባት መልክ በሚሰጥ በሳይንሳዊ የእድሜ መቅጫ “bio-weapons” እድሜውን ማሳጠር ከእነዚህም ያለፈውን እርስ በእርሱ እንዲጫረስ የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ……… ወዘተረፈ የበለጸጉ አገሮች አጸያፊ ሰይጣናዊ ሸፍጣቸውን በአይናችን አሳይተውናል፣በጆሮአችን አሰምተውናል እንዲሁም በብዙ መረጃዎች ተደግፈው በግልጽ ቀርበውልናል::ይህንን እያወቅን ነው እኛም አይናችንን ጨፍነን እና ጆሮአችንን ከድነን “ነጮቹ ረሀብ እና በሽታ እንዲሁም ሞት በኢትዮጵያ እንዲኖር አይፈልጉም!” የምንለው:: ሌላው የተነሳው ነገር “በረሀቡና በጠኔው ምክንያት የሞተ ሰው የለም” በጀመሪያ ደረጃ መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር ሁል ግዜ አብሮን በሚኖር በረሀብ እና በጠኔ እንዲሁም በሞት መካከል ልዩነት አለመኖሩን ማወቅ ይኖርብናል ምክንያቱም “ሞት” ማለት ከረሀብ እና ከጠኔ እንዲሁም ከበሽታ መሰቃየት ማረፍ ማለት ነው:: በተአምር እንኳ እንደ እኛ ባለ በድህነት እና በጠኔ ጥጋብ አረንቋ ለሚሰቃይ ህብረተሰብ ከነዚያ የጠኔ ስቃይ ያገገመ ሰው ህሊናው ሁሌም ሊያርፍ አይችልም:: ምክንያቱም እነዚያ አስከፊ የጠኔ ስቆቃዎቹ ዳግመኛ ባለመምጣታቸው ምንም ዋስትና የለውምና ስለዚህም ከ 20 ሚሊዮን በላይ ምስኪን በረሀብ እና በጠኔ ጥጋብ እየተሰቃዩ የሚገኙ ወገኖቻችን አልቅሰን አልቀበርናቸውም እንጂ ከሞቱ ቆይተዋል::አይደለም እንዴ ጓዶች?

    Reply

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Tweets by @Wazemaradio
Skip to toolbar